አሰባሳቢ ትርክትን ለመፍጠርና ህብረ-ብሔራዊነትን ለማፅናት የመምህራን አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፦ -አቶ ማስረሻ በላቸው
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ “ትውልድ በመምህር ይቀረጻል ፤ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል የመምህራን ውይይት እየተካሄደ ነው። የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕረዝደንት ዶክተር ደገላ ኤርገኖ ፤ የዚህ ሀገር-አቀፍ መድረክ ዓላማ የመምህራንን ሀሳብ ለማድመጥና እርስ-በእርስ ለመወያየት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የምትፈጋቸውን በሳልና በማመዛዘን የፈለቁ የምሁራን ሀሳቦችን ለማስተናገድ ታስቦ እንደሆነም አብራርተዋል። መንግስት ለሚሰራቸው ስራዎች…
