“የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ እና በዳውሮ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ዉይይት እየተደረገ ይገኛል ።
የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ሲሳይ እንደገለጹት የተሻለ የሕዝብ ግንኙነት ሥራና አገልግሎት በተጨባጭ መረጃ በማደራጀት ለኅብረተሰቡ ማድረስ እንዲቻል የሚያግዙ ተግባራት ለሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተከናወኑ ይገኛል ። ከዚህ የተነሣ በየደረጃው ለሚገኙ በዳውሮ ዞን ለሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ሥልጠና ተዘጋጅቷል። በሥልጠናው አገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የልማት ሥራዎችና የተመዘገቡ ድሎችን በማስተዋወቅ በኩል ለዘርፉ…
