በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀውን ሞዴል የኦንላይን ፈተና እየወሰዱ መሆኑ ተገለጸ።
በቤንች ሸኮ ዞን የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገለፀ። በዘንድሮው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚዛን ቴፒ ዩንቨርሲቲ እየተሰጠ ያለውን ኦንላይን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሙከራ ፈተና አሰጣጥ ሂደት የዩኒቨርስቲው የዞንና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት ጉብኝት ተካሂዷል። በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ…
