በክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተመሩ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የገብረፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታልን ጎበኙ::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በተከበሩ ወንድሙ ኩርታ የተመራው የም/ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ቡድን በቦንጋ ከተማ የሚገኘውን የገብረፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታልን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። የጉብኝቱ ዓላማ በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምልከታ በማድረግ የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት ለተሻለ አገልግሎት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ላይ ያተኮረ እንደሆነ አፈ ጉባኤው ገልጸዋል። በጉብኝቱ ወቅት…
