በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተመራው ልዑክ ቦንጋ ከተማ ገባ።

ልዑኩ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጎጀብ ከተማ ሲደርስ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የካፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ልዑካኑ በቆይታው የፈረንሳይ ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ሰነ-ስርዓት በቦንጋ ከተማ በማካሄድ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልል ርክክብ እንደሚደረግ ተጠቁሟል። በቦንጋ ከተማ ዛሬ ከሰዓት የፓናል ውይይት…

Read More

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም እየገመገመ ነዉ::

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 6ቱ ዞኖች የተወጣጡ የትምህርት ዘርፍ አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያሳተፈ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የሚገመግም መድረክ በተርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። አሁን ላይ የሚታየውን የትምህርት ስብራቶችንና ኪሳራን በመጋፈጥ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር ተገቢ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ…

Read More

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሊበን ጭቋላ ወረዳ የአሸባሪው ሸኔን ሁለት ሻምበሎች ከነ ሻምበል አዛዦቻቸው ተደመሰሱ

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሊበን ጭቋላ ወረዳ የአሸባሪው ሸኔን ሁለት ሻምበሎች ከነ ሻምበል አዛዦቻቸው መደምሰሳቸውን የጉና ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት አስታወቀ፡፡ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ወረዳ አዋሽ ወንዝን ተከትሎ ባሉ ቀበሌዎች እና በዝቋላ አቦ ተራራማና ጫካማ አካባቢ ተሰግስጎ የሽብር ሴራ ሲፈፅም የነበረው አሸባሪ ሃይል ከጥቅም ውጭ መደረጉ ተገልጿል። የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል…

Read More

በግብርና ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመድገም ትልቅ ትልም አለን-ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር)

በግብርና ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመድገም ትልቅ ትልም አለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን በኦሮሚያ ክልል እና በሲሲኢሲሲ መካከል በተደረገ በገዳ የኢኮኖሚ ዞን የሉሜ ነፃ የንግድ ቀጠና ማልማት ስራ የመግባቢያ ስምምነት መርሃግብር አስጀምረዋል። ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ የገዳ ኢንዱስትሪ ዞን የሀገራችን…

Read More

ngj

በግምገማ መድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ እንደተናገሩት ጉዳዩ የገፅታ ግንባታና የዞኑን የስፖርት ዘርፍ ለማነቃቃት በዚህም አካባቢያችንን ለዓለም አጉልቶ ለማሳየት ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ እንደ ዞን ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እስከ ታችኛው ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ተሣታፊዎች በአግባቡ መለየታቸውን ተናግሯል። የቦታ ዝግጅት፣የፓናል መወያያ አዳራሽ የማዘጋጀትና የማስዋብ ሥራ፣ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችል የመስተንግዶና የተሽከርካሪዎች ዝግጅት በስፋት የተሰሩ…

Read More

የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ የራሱን ገቢ አመንጭቶ ራሱን እያስተዳደረ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::

የቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን እንደገለፁት ኮሌጁ የራሱን ገቢ አመንጭቶ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከስራና ክህሎት ሚኒስተር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እየተሰራ ነው፡፡ ኮሌጁ ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ በመማር ማስተማር፣ በቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ላይ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አቶ ካሳሁን አስታውሰው አሁን መሬት ላይ ያሉት ሀብቶችን በማዘመን ኮሌጁ የውስጥ ገቢውን…

Read More

የቤተሰብ ጤና ቡድን ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ::

የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር የቤት ለቤት የቤተሰብ ጤና ቡድን ተግባር ይበልጥ ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሂዷል የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዮሐንስ በንዲ በመድረኩ እንደገለጹት የከተማውን ህዝብ ጤናን በመጠበቁ ረገድ በሚሰሩ ስራዎች ሁሉ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አደርገው እንደሚሰራ ተናግረዋል። ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብን በመፍጠር የልማት ስራውን በማሳለጥ ለራሱን ለሀገሩ የሚበቃ ዜጋ…

Read More

በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸም እና ወረርሽኝ ቁጥጥር ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍ ሊደረግ ነው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮበጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸም እና ወረርሽኝ ቁጥጥር ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም የድጋፍ ስራ ለሚሰሩ የቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ኦሬንቴሽን ሲሰጡ እንደገለጹት የጤና ኤከስቴንሽን ፕሮግራም አተገባበርን በማጠናከር እና ስራው በተቀጣጠለ አኳን እንዲሰራ በክልሉ በሶስት ክላስተር ከተሞች የጤና ኤከስቴንሽን ባለሙያዎች ግምገማ ነክ ስልጠና…

Read More

አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ሀገር የመገንባት ራዕይን ከግብ ለማድረስ ሁለንተናዊ የልማት ዕቅዶቻችን ሳይቆራረጡ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

የፌደራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማ ዛሬ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ከመስክ ምልከታ የተገኙ ሪፖርቶችን ጨምሮ የተቋማት አፈፃፀም ጠለቅ ባለ እና በተደራጀ መልኩ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ዕቅዶች መሬት ላይ ወርደው ሲተገበሩ ምን ውጤት አመጡ፣ በትግበራ ሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮች ምን ይመስላሉ፣ እንዲሁም በቀጣይ በመረጃ እና በትንተና የተደገፈ አካሄድ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል በመድረኩ ተነስቷል፡፡ በሱፐርቪዥኑ ሪፖርት በመልካም ጅማሮ የታየው ዋንኛው…

Read More

ወደ ማህበረሰቡ ለሚቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች የጤና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

የጤና ሚኒስቴርና የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ወደ ማህበረሰቡ ለሚቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። መንግስት የቀድሞ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽኑ እየሰራ ይገኛል፡፡ በተለይም የቀድሞ ታጣቂዎች ትጥቅ ከማስፈታት ጀምሮ መልሶ የማቋቋም ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል። የቀድሞ ታጣቂዎችን ለሰላምና ምርታማነት ለማዘጋጀትም ማህበራዊ…

Read More