ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዩጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዩጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ጉብኝቱ እየተካሔደ ያለው በዩጋንዳ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም እና የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የመጀመሪያ ልጅ በሆኑት ጄኔራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ እና የልዑካን ቡድናቸው ዩጋንዳ ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በዩጋንዳ ምድር ኃይል ኮማንደር ሌተናል…
