ስራ ፈጣሪ ዜጋን ለማፍራት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ትምህርት ኮሌጅ ያለው ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ
የቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 89 ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡ በዳውሮ ዞን ከሚገኙ አምስት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መካከል የቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አንዱ ሲሆን ኮሌጁ በ2013 ዓ.ም ወደ ስራ መግባቱን ኮሌጁ ዲን አዲሱ ዘካሪያስ ገልፀዋል። በዚህም በሰባት ትምህርት ዘርፎች በርካታ ሰልጣኞች እያሰለጠነ ሲሆን በዛሬው ዕለት በአይስቲና (ICT) እና በኮንስትራክሽን ሙያ ዘርፍ በመደበኛና በማታ…
