ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ 502ኛ ህዳሴ ኮር የመከላከያ ሰራዊት ሬጅመንት መኖሪያ ካምፕ መርቀው ከፈቱ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የዳሎል ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ 502ኛ ህዳሴ ኮር የመከላከያ ሰራዊት መኖሪያ ካምፕ መርቀው ከፍተዋል። ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የሀገርን ዳር ድምበር በማስከበር ታሪክ የማይረሳው ገድል ፈፅመዋል ብለዋል። ክልሉ ከተደራጀ…

Read More

በዘንድሮው የመኸር እርሻ እስካሁን 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በዘር ተሸፍኗል – ግብርና ሚኒስቴር

በ2016/17 የምርት ዘመን በመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው 20 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በዘር መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በዘር ከተሸፈነው ውስጥ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታሩ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ የለማ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ከበደ ላቀው ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በ2016/17 የምርት ዘመን በመኸር…

Read More

በቀጣዮቹ ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል

በቀጣዮቹ አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡ ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ እየተጠናከረ እንደሚሔድ ገልጿል፡፡ የሚጠበቀው እርጥበት የመካከለኛ ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት ፣በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች የውሃ ፍላጎትን ለማሟላት እንደሚረዳ የትንበያ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በዚሁ…

Read More

የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተሽለመ

ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ለከተሞች እንደሀገር ባዘጋጀው ምዘና መስፈርት መሠረት ተመዝነው ከ26 ከተሞች አንዱ በመሆን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ሽልማቱን አግኝቷል። የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ከተለያዩ ከተሞች ከተወጣጡ ከአቻ ከተማ ከንቲባዎች ጋር ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ጉብኝት የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ የተሳተፉ…

Read More

አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የሀገር ፍቅርን ደርባችሁ፣ ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት መስራት ይገባችኋል፦አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት እንዲወከሉ አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፥ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የሀገር ፍቅርን በማስቀደም በህዝብ የታመነ አደራን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አምባሳደሮቹ እውቀትን ከሀገር ፍቅር ደርበው፣ ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት የአገልጋይነት ክብርን ማሳየት እንደሚገባቸውም አምባሳደር ታዬ ገልፀዋል። ስልጠናው ሀገሪቱ ከምታራምደው የውጭ ግንኙነት…

Read More

አሁንም ትኩረት የሚፈልገዉ የወባ በሽታ

ኢትዮጵያ ሀገራችን ለበርካታ ዘመናት መከላከል ላይ መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ስትተገብር እንደቆየችና በርካታ የሆኑ ለውጦች በጤናው ዘርፍ መመዝገባቸው ይታወሳል ። ከዚህም መካከል የወባ በሽታን በእጅጉ ለመቀነስ ብሎም ለመቆጣጠር በሚያስችል ደረጃ ላይ ተደርሶ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የወባ ስርጭት በስፋት እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቅሳሉ ። ከነዚህም ክልሎች የደቡብ…

Read More

በክልሉ ሶስት ከተሞችን ተጠቃሚ ያደረገ በከተሞች የተቋማትና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አንድ (UIIDP 1) አፈጻጸም ተገመገመ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች ተቋማትና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ምዕራፍ አንድ (UIIDP 1) ፕሮግራም አፈጻጸም ማጠቃለያ ግምገማ መድረክ በሚዛን አማን ተካሂዷል ። በመድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኢንጂነር የማታለም ቸኮል የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊው በከተሞች እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥርን መሸከም የሚያስችል አቅም ያለው ከተማን ለመፍጠር…

Read More

ሀገራዊ ምክክሩ በውይይት የጋራ መግባባት ለመፍጠር ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ፈጥሯል- አምባሳደር መሐሙድ ድሪር

ሀገራዊ ምክክሩ በውይይት ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር፤ ኢትዮጵያ በምክክር ችግሮቿን ለመፍታት የነበሯት በርካታ ዕድሎችና አጋጣሚዎች አምልጠዋት እስካሁን መዝለቋን አስታውሰዋል። በተለያዩ ዘመነ-መንግሥታት ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ሰፊ ዕድል የነበራት ቢሆንም ወደ ተግባር መቀየር ተስኗት መቅረቱንም ይናገራሉ። ለአብነትም…

Read More

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋምና ጥቅማቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሥምምነት አደረገ። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ሥምምነት አድርጓል። በተጨማሪም ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ እንዲሁም ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋርም…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወባ ጫና ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት እየተሰራ ነው።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወባ ጫና ያለባቸው አካባቢዎች ተለይተው የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት÷ በክልሉ ሁሉም ዞኖች የወባ ስርጭት እንዳለ ጠቅሰው፤ 34 ወረዳዎች ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸው መለየቱን ጠቁመዋል። በክልል ደረጃ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ለ186 ሺህ 133 ሰዎች የወባ በሽታ ምርመራ ተደርጎ 55 ሺህ…

Read More