ባለሀብቶች ያለ ችግር ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የካፋ ዞን አስተዳደር ገለጸ ።
የዞኑ ገበያ ልማት እና እንቨስትመንት መምሪያ በዞኑ ካሉ ባለሀብቶች ጋር የእንቨስትመንት ምክክር ፎረም አካሂዷል። የመምሪያው ሀላፊ ወ/ሮ ታሪኳ ታከለ በዞኑ ወደ 3 መቶ 29 ኢንቨስተሮች መኖራቸውን በመጠቆም በየዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች በትኩረት መስራት ከቻሉ ውጤታማ መሆን ይችላሉ ብለዋል። የእንቨስትመንት ስርጭቱ በሁሉም ወረዳዎች የተዳረሰ ሲሆን የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ከራስ ባሻገር ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነትም መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የዞኑ ዋና…
