በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሜትሮሎጅ መረጃዎችን የሚሰብስብ ጣቢያ እንደሚቋቋም የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ
የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት በመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ የሜትሮሎጅ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያ ማቋቋም ላይ መነሻ ያደረገ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ ከአየር ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎችን በመሰብሰብ በማደራጀትና በመተንተን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል የሚያስችል…
