የተረጂነትንና የጠባቂነትን አስተሳሰብ በመቀነስ በራስ አገዝ በክልሉ የሚታየውን የእርዳታ ፍላጎት ለመሸፈን መስራት ይገባል። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ” ያለመ ክልላዊ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል ። በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በእርዳታ ያደገ ሀገርም ግለሰብም የለም ያሉ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሚያጋጥሙንን አደጋዎችን አቅማችንን በመገንባትና ህዝባችንን በማስተባባር ሊንወጣዉ ይገባልም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ…
