ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ
ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ፅንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑን አረጋግጠዋል። ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች፣ የገጠር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ህዝቡ ”ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ በነቂስ ወጥቶ ላሳየው…
