በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሜትሮሎጅ መረጃዎችን የሚሰብስብ ጣቢያ እንደሚቋቋም የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ

የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት በመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ የሜትሮሎጅ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያ ማቋቋም ላይ መነሻ ያደረገ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ ከአየር ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎችን በመሰብሰብ በማደራጀትና በመተንተን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል የሚያስችል…

Read More

ምሁራን የህዝቡ አጀንዳ አጀንዳችን ከሆነ ከመነጣጠል ፣ ከመገፋፋትና ከመበተን ይልቅ ለአንድ አላማና ለማህበረሰቡ ለውጥ በጋራ ልንሰራ ይገባል ፦ አቶ ሀብታሙ ካፍትን

3ኛው የቤንች ብሔር ምሁራን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት አለም ለዛሬ ስልጣኔ ፣ ዘመናዊነትና ዕድገት የበቃችው በምሁራን የፈጠራ ፣ የጥበብና የምርምር ስራዎች ታግዛ ነው ብለዋል። ዛሬ ላይ በአለማችን እጅግ ሰለጠኑ ፣ በሳይንስና ቴክሎጂ ምጡቅ ሆኑ የሚባሉት ሀገራት ከመሬት ተነስተው ሳይሆን…

Read More

ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ለሀገራዊ ምክክሩ ግብዓት የሚሆን አሻጋሪ ሃሳብ በማመንጨት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ

ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈቱና ለትውልድ የምትመች አገር ለመገንባት የሚያስችል አሻጋሪ ሃሳብ በማመንጨት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ። ” ተመካክረን ኢትዮጵያን እንገንባ፤ እኔም ለሀገሬ እመክራለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ተዋቂ…

Read More

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የተከተለችው መርህ ለቀጣናው የጋራ ተጠቃሚነት ወሳኝ ነው

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የተከተለችው የሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲያዊ መርህ የቀጣናውን ሀገራት ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እያደገ ላለው የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት የወደብ ቁጥርን ማስፋት አስፈላጊ ነው ብለዋል። የባህር በር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ብልጽግና ወሳኝ እንዲሁም ለጎረቤት ሀገራት…

Read More

ደቡብ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ኩባንያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ከፈተ።

ኩባንያው የአገልግሎት አሰጣጡን የማዘመንና ቅርንጫፍ ጸ/ቤቶችን በየክልሎች የመክፈት ጉዳይ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሏል። ኩባንያው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በዛሬው ዕለት በይፋ ከፍቷል። በክልሉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት መክፈቻ ስነ_ስርዓትን ተከትሎ የኩባንያውን የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ባቼ በ4 ክልሎች በ67 ከተሞች ተደራሽ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል ። ኩባንያው በክልሎቹ…

Read More

ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው ተጠቆመ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የታርጫ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እና ሶሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክብርት ሚኒስትር ደኤታ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ወርዶ ማየታቸው…

Read More

ባለፉት ሶስት ወራት አምራች ኢንዱስትሪዎች 816 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት ችለዋል

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባለፉት ሶስት ወራት አምራች ኢንዱስትሪዎች 816 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች ማምረታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። የሀገር በቀል ኢኮኖሚ እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ትግበራ ለአምራች ኢንዱስትሪው ያመጣው መልካም ዕድል፣ ተግዳሮት እና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ የመንግሥትና የግል ዘርፉ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤…

Read More

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹዌ ቢንግ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይቀያየር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው ጥረት የቻይናን ድጋፍ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (FOCAC) የተቀመጡ ግቦችን ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ…

Read More

የትምህርት ሴክተር ማነቆዎችን ለመፍታት እየተተገበረ ያለው ማሻሻያ አውንታዊ ለውጥ እያሳየ ይገኛል፦ ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

መንግሥት የትምህርት ሴክተር ማነቆዎችን ለመፍታት እየተገበረ ያለው ማሻሻያ አውንታዊ ለውጥ እያሳየ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ”የትምህርት ጥራት እምርታ ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መርህ ቃል በተዘጋጀው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ላይ ነው። ትምህርት የሀገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎች በእውቀት፣በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጸው የሚወጡበት…

Read More

የክልሉ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል

”የትምህርት ጥራት እምርታ ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መር ቃል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው 1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የ1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ክልላዊ የትምህርት ልማት ሥራዎች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድም ተገልጿል። በጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር…

Read More