በማህበር ተደራጅተው በከብት እርባታ ላይ የተሰማሩ ውጤታማ ሥራ እየሠሩ መሆኑ ተገለጸ
በዳውሮ ዞን በታርጫ ከተማ አስተዳደር በለማት ትሩፋት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ የከተማው ከንቲባ የሆኑት አቶ ዳዊት ወንድሙ ገልጸዋል ። የለማት ትሩፋት የስነ ምግብ ስርዓትን ከማሻሻልና ከማጠናከር አልፎ የስራ ዕድልን በመፍጠር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የገለጹት የከተማው ከንቲባ ከነዚህም በዶሮ እና እንስሳት እርባታ፣ በጓሮ አትክልትና በበጋ መስኖ የለማ በቆሎና እየለማ ያለው ስንዴ ልማትን ለአብነት አንስተዋል ። በማህበር…
