በፕላን የተሰሩ የገጠር ማዕከላት ለዘላቂ የከተማ ልማት ምሶሶ ናቸው – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
የተቀናጀ የገጠር ማዕከላት ልማት የንቅናቄ መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የተገኙት ሚኒስትሯ በፕላን የተሰሩ የገጠር ማዕከላት ለዘላቂ የከተማ ልማት ምሶሶ መሆናቸውን ተናግረዋል። የመንገድ ግንባታን ከገጠር ቤቶች አቅርቦት ጋር በማሳለጥ፣ የባለሙያዎችን አቅም በመገንባትና የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። መንግሥት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላና ከሰብዓዊ መብቶች መካከል…
