ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ።
በውይይቱም የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በምርጥ ዘር አቅርቦት ለማሳደግ እንዲሁም ዘርፉን በማዘመን ረገድ እስካሁን ሲያከናውን በቆየባቸው ጉዳዮች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ዓላማ ያደረገ ነው። የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በክልሉ ቦንጋ ከተማ የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና ሜካናይዜሽን ማዕከል በመገንባት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተለያዩ ምርጥ ዘር ምርትና አቅርቦት፣የግብርና ሜካናይዜሽን (ማሽነሪ አቅርቦትና ጥገና አገልግሎት፣ የግብርና ግብዓትአርቦትና…
