የአርብቶ አደሩን ሕይወት በዘላቂነት በመቀየር የተረጋጋ ኑሮ እንዲመራ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የሚሠሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል። በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የሚሠሩ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ የልማት እና የፕሮጀክት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና በዘላቂነት የተረጋጋ ኑሮ እንዲመሩ በክልሉ መንግሥት በኩል ሰፊ ስራ እየተሠራ መሆኑን የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኋላፊ አቶ መቱ አኮ ተናግረዋል። ሱሪ ወረዳ ለተለያዩ የሰብል…

Read More

ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ለመዘርጋት በየደረጃው የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ተቋማት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸዉ መስፍን ወዳጆ (ዶ/ር) ገለጹ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች በዳውሮ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማጠቃላያ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓል። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በዞኑ የሚገኙ ኮሙኒኬሽን ተቋማትን ድጋፋዊ ክትትል ሲያደረጉ ቆይተው ዛሬ በዞን ማዕከል የዞኑን የ2018 የግማሽ አመት አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠቃሏል። ዶ/ር መሰፍን በዚሁ ወቅት እንደገለፁት በሕዝቡና መንግሥት መካከል ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ…

Read More

በክልሉ የሚተገበረው የኤሌክትሮኒክስ ቫውቸር የዲጂታል አሰራር ሥርዓት ውጤታማ እንዲሆን ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ ይገባል፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት እና ዕዳ አመላለስ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ መሠረታዊ ጉዳዮችን የሚቀርፍ የኤሌክትሮኒክስ ቫውቸር (E-VOUCHER) ሥርዓት የግብርና ግብዓት ሽያጭ ይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያ መረሐ- ግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። የማስጀመሪያ መረሐ-ግብሩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በጋራ አዘጋጅነት ነው የተከናወነው። በመረሐ-ግብሩ በክልሉ ቀደም ሲል በካፋና በቤንች ሸኮ ዞን በሦስት ወረዳዎች…

Read More

መንግስት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ዜጎች የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በማድረግ የምግብ ሰብአዊ ድጋፍ እያቀረበ ይገኛል – የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

መንግስት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በማድረግ የምግብ ሰብአዊ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ህፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃቀዮችም የተሟላና ያልተቆራረጠ የምግብ ሰብአዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ኮሚሽኑ ገልጿል። ለተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገላቸው አይደለም የሚለው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑንም ነው ያመለከተው። የኢትዮጵያ አደጋ…

Read More

በዞኑ ያሉ እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ታሪካዊ ሀብቶችን ጠብቆ ለዓለም ማስተዋወቅ እንደሚገባ ተገለጸ

ይህም የተገለጸው በቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተመራ “ቱር ኢትዮጵያ” ልዑክ በካፋ ዞን የቡና መገኛ የሆነቹን ዴቻ ወረዳ ማኪራ በመሄድ በጎበኙበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪስት መስህቦችን በመለየት፣ ለማልማትና ለማስተዋወቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በቱሪዝም ሚኒስቴር የመረጃ ሲኒየር ባለሙያ አቶ አለማየሁ ወርቀዣ ገልጸዋል ለቱሪዝም ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የገቢ ምንጭ እና የስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት 5 ወራት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ልማት ገብተዋል አለ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ።

የቢሮው ም/ሃላፊና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ እንዳሉት ÷ በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማነቃቃት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ ባለፉት 5 ወራት 42 ባለሃብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመው ÷ ወደ ሥራ ከገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል 34ቱ በግብርና ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም አምስቱ በአገልግሎት ዘርፍ እና ሦስቱ ደግሞ በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራታቸውን ነው ያስረዱት፡፡ በፕሮጀክቶቹ ከ35 ሺህ…

Read More

የመረጃ ተደራሽነቱን ለማስፋት የታየው ቅንጅታዊ አሰራር አበረታች መሆኑ ተገለጸ

ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተውጣጣ የድጋፋዊ ክትትል ቡድን በክልሉ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ላይ ድጋፍዊ ክትትል አድርገዋል ። በዚህም በቅርብ ጊዜ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እየሠጠ የሚገኘው የቤንች ሸኮ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን አንዱ ነው ። ምንም እንኳን በቅርብ ጊዜ ተቋሙ የተደራጀ ቢሆንም የመረጃ ተደራሽነትን ሁሉ አቀፍ ለማድረግ የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች አበረታች እንደሆነ በመስክ ምልከታው ወቅት የክልሉ…

Read More

የሚዛን አማን ከተማ ልማት የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነትና ዘመናዊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተከናወነ ነው

የሚዛን አማን ከተማ ልማት የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነትና ዘመናዊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገለጸ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብዝኃ ከተሞች አንዷ ሚዛን አማን ከተማ ለቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ ከተማ እየሆነች ትገኛለች። የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ኢንጂነር ሰሎሞን ሌዊ፤ በመደመር መንግስት እይታ የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ውብ ጽዱና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን…

Read More

የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት እና ዕዳ አመላለስ አስተዳደር ሥርዓትን የማዘመኑ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል ፦ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት የኤሌክትሮኒክስ ቫውቸር (E-VOUCHER) ሥርዓት የግብርና ግብዓት ሽያጭ ይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በማስጀመሪያው የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደተናገሩት እንደሀገር የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳለጥ በተለያዩ ዘርፎች በተጀመሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ናቸው። ይህን ሀገራዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓትን የማሳለጡ…

Read More

ባለፉት 5 ወራት የትራፊክ ደንብ በተላለፉ 17 ሺህ 951 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር አስናቀ አፍቴ የትራፊክ አደጋ መከላከልና የታርፍ ቁጥጥር ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ ውጤታማ ተግባራት በማከናወን ላይ እንገኛለን ብለዋል። ከዚህ በፊት የታርፍ ቀጥጥሩም ይሁን የትራፊክ አደጋ መከላከሉና የድጋፍና ክትትል ሂደቱ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በርካታ ውስንነቶች ያለው መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ይህንን ለመቅረፍ ባለፉት ስድስት…

Read More