ኢትዮ-ህንድ
ኢትዮጵያና ህንድ ከሁለት ሺህ ዓመታት የተሻገረ ሁለንተናዊ ግንኙነት እንደነበራቸው የተለያዩ መዛግብት ያስረዳሉ። ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮም በርካታ የህንድ ተወላጆች ኢትዮጵያን የኑሮ ምርጫቸው እንዳደረጉ የሚያመለክቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ። በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መካከል በነበሩት ዓመታት በርከት ያሉ ሕንዳውያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡ በፈረንጆቹ 1948 ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረተች…
