ከእጥፍ በላይ ምርት የሚሰጠው ‘መልካም’ የተሰኘው የማሽላ ዘር ለአርሶ አደሩ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ
የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ የአካባቢውን አርሶ አደሮችና የክልሉን የማሽላ ዘር ፍላጎት ለማሟላት “መልካም” የተሰኘ ምርጥ የማሽላ ዘር እያባዛ መሆኑን አስታወቀ። ማዕከሉ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኘው የኦትዋ ንዑስ ምርምር ጣቢያ እያካሄደው ባለው የዘር ብዜት፣ በሄክታር እስከ 60 ኩንታል የሚደርስ ምርት የሚሰጠውን ይህን ዝሪያ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና…
