ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት አስጀመሩ

ዛሬ ስራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፣ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሰራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ስርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ ነው። ‎አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ስርዓት ያለው ሲሆን፣ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችንም አካቷል።…

Read More

54ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 54ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚውል ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የሰማንያ ሚሊዮን (80,000,000) ዩሮ ብድር ስምምነት ነው፡፡ ሁለተኛው ለአነስተኛ የገጠር ገንዘብ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም የሚውል ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት…

Read More

መገናኛ ብዙኃን የወል ትርክት ግንባታ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን መገናኛ ብዙኃን የሀገር ግንባታ ሂደትን ለማጠናከርና የወል ትርክትን ለመገንባት በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል። ባለስልጣኑ ከሚዲያ ተቋማት ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር “መገናኛ ብዙኃን ለሀገር ግንባታ እና ለማህበረሰብ አመለካከት ቀረጻ” በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት እያካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መገናኛ ብዙኃን በሚሰሯቸው ስራዎች መሻሻሎች መኖራቸውን…

Read More

ከዕዳ ጥገኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት

ኢትዮጵያ ከአሳሪውና ከአባካኙ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሥርዓት ወጥታ፣ በዕውቀትና በዲሲፕሊን የሚመራ ጠንካራ የኢኮኖሚ መዋቅር መገንባት ችላለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገራዊ ጸጋዎችን ወደ ላቀ ምርታማነት ለመቀየርና የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የጀመራቸው ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎች፣ ዛሬ ላይ ሀገራችንን በዓለም ፈጣን ዕድገት ካላቸው አሥር ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርገዋታል። አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተለያዩ ውስብስብ ሀገራዊና…

Read More

ከክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 302 ነጥብ 27 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ቀርቧል

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 302 ነጥብ 27 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ። ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ወልያብ (ዶ/ር) እንደገለጹት ኤጄንሲው በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 262 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ…

Read More

የኪነጥበብ ሥራዎችን በማበረታታት ለሀገር መንግሥት ግንባታ የሚያበረታቱ አስተዋጽኦ ማጉላት እንደሚገባ ተገለጸ።

በሰዓሊ አብረሃም ተስፋዬ የተዘጋጁና የካፋን ነገሥታት ታሪክ፣ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓትና የማኅበረሰቡን ጥንታዊ አኗኗር የሚዘክሩ የስዕል አውደርእይ በቦንጋ ከተማ ተከፍቷል። የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን አሰናስነው የሚይዙ በመሆናቸው ለማኅበረሰብ የታሪክ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ነው በአውደርዕይ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የገለጹት። ኪነ-ጥበብ የአንድን ማኅበረሰብ ቱባ ባህል፣ ዕሴት እንዲሁም…

Read More

ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምቹነት ለመፍጠርና የተሳካ ምርጫ ለማካሄድ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ስሜት እየተሰራ ፦ አቶ ፍቅሬ አማን

የክልሉ የምርጫ አብይና ንዕስ ኮሚቴ የእስካሁኑ የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በአብይና ንዕስ ኮሚቴው በእስካሀኑ በቅድመ ምርጫ አተገባበር ዙሪያ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል። በምርጫ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን ምቹነት ለመፍጠርና የተሳካ ምርጫ ለማካሄድ…

Read More

በበጀት ዓመቱ 9 ወራት የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት መከናወናቸዉን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ

‎ቢሮው የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣው መግለጫ ስጥተዋል። ‎መግለጫውን የሰጡት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ወልደማርያም በዛብህ በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ፥ በመሰረተ ልማትና በፍትህና አስተዳደር ዘርፎች የህብረተሰቡን ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፎች ተለይተው ተግባራዊ መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ‎ግብርና የክልሉ ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም በመሆኑ የአርሶ…

Read More

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አቭዬሽን ሴኩዩሪቲ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ አቭዬሽን ሴኩዩሪቲ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አፅድቋል። የማሻሻያ አዋጅ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ስራ ላይ የቆየውን አዋጅ የሚተካ ሲሆን፣ በዘርፉ የታዩ አዳዲስ የደህንነት ስጋቶችንና የቴክኖሎጂ ለውጦችን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ተገልጿል። በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈቲህ መሀዲ…

Read More

የሕብረት ሥራ ማህበራት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

የሕብረት ሥራ ማህበራት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛውን ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ በተለያዩ ከተሞች በማካሄድ ላይ ይገኛል። በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው መድረክ…

Read More