የክልሉን ሕዝቦች የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስመዝገባቸውን ቢሮው አስታወቀ

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት፣ የወባ በሽታ ጫና መቀነስና የጤና መድህን ተደራሽነትን በማረጋገጥ ረገድ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ። ​የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት፤ በክልሉ የእናቶችንና የሕፃናትን ጤና ለመጠበቅ በተደረገው ጥረት የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ከፍተኛ ውጤት…

Read More

sd

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ኢኮኖሚያዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ የጸደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን ከፈረንሳይ ግምጃ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ በማስመልከት መክረዋል፡፡ በተጨማሪም ውይይቱ ሀገራቱ የልማት ትብብራቸውን ማሳደግ፣ የማክሮኢኮኖሚ ትብብር ስለሚያድግበት ሁኔታ…

Read More

ቀጣዮቹ 90 ቀናት የአምስት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም የሚለካባቸው ወሳኝ ምዕራፍ በመሆናቸው በልዩ ትኩረት ሊመሩ ይገባል፦ ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የመንግሥት እና የብልፅግና ፓርቲ የተግባር አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ ገምግሟል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ቀጣዮቹ ዘጠና ቀናት በአምስት ዓመቱ ለህዝቡ የተገባ ቃል አፈጻጸም የሚመዘንበት በመኾኑ በልዩ ትኩረት ሊፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል። በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በክልሉ በሁሉም መስኮች ካለፉት ዓመታት…

Read More

‎የክልሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በማልማት ኢኮኖሚ የማመንጨት አቅማቸውን ማሳደግ ላይ ትኩረት መደረጉን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ገለፀ።

‎የክልሉ መንግስትና የፓርቲ 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ‎በመድረኩ የክልሉን መንግስት የ9 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማትና ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በተለይ የኢኮኖሚ ክላስተር አፈፃፀሙን በዳሰሰው ሪፖርታቸው ግብርና የክልሉ ትልቁ ፀጋ በመሆን ዘርፉን በማሻሻልና በማዘመን የህብረተሰቡን…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት አዳዲስ ኤርፖርቶችን በቅርቡ ሊያስመርቅ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ አራት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶችን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያደቻ በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ 23 ኤርፖርቶች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኝ ሲሆን፤አራት ተጨማሪ ኤርፖርቶች በቅርቡ ይመረቃሉ፡፡ እነዚህም ነጌሌ ቦረና፤ ሚዛን አማን፤ ጎሬ መቱ እና ደብረ ማርቆስ ኤርፖርት መሆናቸውን ጠቅሰው፤…

Read More

በክልሉ መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ ወረቅት አልባ በሆነ ቴክኖሎጂ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ተገለጸ

ሀገር አቀፍ የመንግስት ሰራተኞች ፐርሶናል መረጃ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ መድረኩ በልዩ ሁኔታ የሚፈጸም ተግባር ተልዕኮን ለማከናወን ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል። ባለፉት 8 የለውጥ ዓመታት ከመጡ መሠረታዊ ለውጦች አንዱ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፦

ዛሬ ጠዋት የስራ ዘመኑን ሶስተኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገም ጀምረናል። ‎ለእድገት አመቺ ካልነበረው እና በደካማ የተቋማት እና የፖለቲካ ማዕቀፍ ፣ በታጠረ የግል ዘርፍ ተሳትፎ እንዲሁም ውጤታማ ባልነበረ የቁጥጥር ከባቢ ከሚገለጠው የኢኮኖሚ መልክ ወጥተናል። የግሉ ዘርፍ ደካማ ውድድር ውስጥ ነበር፤ በመንግሥት ሥር የነበሩ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው የንግድ…

Read More

የ9 ወራት የመንግሥትና ፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ​መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ በመድረኩ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ እንደገለጹት፤ በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት…

Read More

በወቅታዊ ጉዳዮች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በውይይቱ መግቢያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፥ የብልፅግና ፓርቲ አባልና አመራሩ ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር በሚያስችል ስትራቴጂካዊ የመሻገሪያ አቅጣጫዎችን በቁርጠኝነት እንዲተገብሩ ጠይቀዋል። የብልፅግና ፓርቲ በየጊዜው ሀገራችንን የሚገጥሙ ፈተናዎችን የመሻገሪያ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ወደ ዕድል በመቀየር ኢትዮጵያን…

Read More

የኃይማኖት ተቋማት መገናኛ ብዙኃን ለሰላምና አብሮነት በኃላፊነት ስሜት መስራት ይገባቸዋል

የኃይማኖት ተቋማት መገናኛ ብዙኃን ለተከታዮቻቸው ኃይማኖታዊ አስተምህሮን ከማስረጽ ባሻገር ለሀገር ሰላምና አብሮነት በኃላፊነት ስሜት መስራት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ገለጹ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ባለፉት ሶስት ወራት በኃይማኖት ተቋማት መገናኛ ብዙኃን ላይ ያደረገውን የይዘት ስርጭት ክትትልና ግምገማ ውጤት ይፋ ማድረጊያ መርሀ ግብር አዘጋጅቷል። “የኃይማኖት ተቋማት የመገናኛ ብዙኃን ለሰላምና አብሮነት” በሚል…

Read More