መንግሥት ለዜጎች ሕይወት መሻሻል የቀረጻቸው ፕሮግራሞች በውጤት ሊመሩ ይገባል- ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ለዜጎች ሕይወት መሻሻልና ለተመጣጠነ ሥርዓተ ምግብ መረጋገጥ የቀረጻቸው ፕሮግራሞች፣ ውጤት ተኮር በሆነ መንገድ ሊመሩና ሊተገበሩ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን የገለጹት፣ የክልሉ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ዩኒት የሰቆጣ ቃል ኪዳን ሥራዎችንና የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት አፈጻጸምን በገመገሙበት ወቅት ነው። በመድረኩ ላይ…
