በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካነሷቸው ጥያቄዎች፡-
የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛና ቋሚ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እየጎዳ ይገኛል፤ በ2018 ግማሽ ዓመት አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴያችን ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና የቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ? የምርታማነትን ችግር ለመፍታትና አጠቃላይ የስራ ባህልን ለማሻሻል ምን መሰረታዊና ስር ነቀል መፍትሔ እየተወሰደ ነው፤ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ…
