የክልሉ ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP)የበጀት ድጋፍ በፕሮግራሙ ለታቀፉ ወረዳዎች የመኪና ድጋፍ አደረገ

Spread the love

የክልሉ ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP)የበጀት ድጋፍ በፕሮግራሙ ለታቀፉ ወረዳዎች የመኪና ድጋፍ አደረገ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP)የበጀት ድጋፍ በፕሮግራሙ ለታቀፉ ወረዳዎች የተገዙ ተሽከርካሪዎች የርክክብ እና ቀጣይ አቅጣጫ መስጫ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP)የበጀት ድጋፍ የተገዙ 15 መኪናዎች በፕሮግራሙ ለታቀፉ ለ15 ወረዳዎች ድጋፍ አድርጓል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የክልል፣ የስድስቱም ዞኖች የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እና በፕሮግራሙ የታቀፉ ወረዳዎች የፕሮግራሙ አስተባባሪዎችና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት መኪናዎቹን ርክክብ አድርጓል።

በርክክቡ ወቅት አቶ ማስረሻ በላቸው እንደገለጹት፤ የክልሉ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተለያዩ የግብርና ሥራዎችን በመደገፍ እና የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን እየደገፈ ያለ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በክልላችን በ15 ወረደዎች እና ከ330 በላይ ቀበሌዎችን በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ታቅፈው ተጠቃሚ እየሆኑ እንዳለ ጠቁመው ፕሮግራሙ ለነዚህ ወረደዎች ተደጋጋሚ የሆነ ድጋፎችን እያደረገ ማምጣቱን አንስተዋል፡፡

ፕሮግራሙ አርሶና አርብቶ አደሮች ከነበረው ኀለ የዝናብ ጥገኝነት ላይ መሠረት ያደረገ የአስተራረስ ዛዴ ተላቆ መስኖ እንዲጠቀም የምያስችል ድጋፍ ያደርጋል ያሉት አቶ ማስረሻ ከሚመረተው ምርት አርሶና አርብቶ አደሩ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ የተለያዩ መጋዘኖችን በመገንባት የግብርና ገበያ ልማት በማቀላጠፍ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ዛሬ ርክብክብ የተደረጉ 15 የመኪናዎች ድጋፍም በክልሉ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ለታቀፉ ወረዳዎች የግብርና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን በማሳካት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እና በፕሮግራሙ የታቀዱ ተግባራት ለማሳካት ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።

በየጊዜው በፕሮግራም የሚመጡ የመኪና እና ሌሎች ድጋፎች ለታለመለት ዓላማ ከማዋል ሰፊ ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመው ዛሬ ለወረዳዎች ድጋፍ የተደረጉ መኪናዎች ለታለመለት ዓላማ ላይ እንዲውልና የግብርና ልማት ሥራዎችን ብቻ እንዲደግፍ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) አስተባባሪ አቶ ወንደሰን ሁሴን እንደተናገሩት፤ የፕሮጀክቱን አላማ በታቀደለት ጊዜ ከግብ በማድረስ የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የሎጅስቲክስ አቅርቦትን በመስራት ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዛሬ ርክብክብ የተደረጉ ተሽከርካሪዎች ከሚፈለገው አላማ ውጭ ለጥቅም እንዳይውሉ ጠንካራ ክትትል የሚደረግ መሆኑን አንስተው ወረዳዎችም ድጋፉን ለታለመለት አላማ ማዋል እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል ፡፡

በርክክቡ ላይ አስተያየት የሰጡ አካላትም የተደረገው ድጋፍ የፕሮግራሙንም ይሁን አጠቃላይ የግብርና ልማት ስራዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አንስተው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

📌በትሬድስ

https://www.threads.com/@southwest_communications

📌በብሉ ስካይ

https://bsky.app/profile/swc79.bsky.social

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *