Getenesh Gebeyehu

በበርሊን ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀመረ::

በጀርመን በርሊን በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን (ITB) ጀምሯል። ይህ ኤግዚቢሽን በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ካምፓኒዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው። የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው፤ ኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነቻቸው ያሉ የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦችን እያስተዋወቁ ይገኛሉ። በተለይም…

Read More

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ተጀመረ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል። ግምገማው አራቱን የአስተዳደርና ፍትህ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን በተመለከተ በቀረቡ አፈፃፀሞች ላይ በማተኮር መጀመሩን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሰል የግምገማ መድረኮች በመንግሥት ተቋማት የመፈፀም ባህልን ለማዳበር የጀመሯቸው መሆናቸው ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Read More

የሸካቾ ብሄረሰብ የባህላዊ አስተዳደር መዋቅር መሪ በዓለ ስመት ተካሄደ።

የሸካቾ ብሄረሰብ የባህላዊ አስተዳደር መዋቅር ንግሥና ስነስርዓት በሸካ ዞን የነገሥታት መናገሻ በሆነችሁ ጥንታዊቱ የአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ተካሂዷል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካሉት ስድስት የአስተዳደር መዋቅሮች አንዱ የሆነው የሸካ ዞን የድንቅ ተፈጥሮ፤ የብዙ ታሪክና ባህላዊ ዕሴት ባለቤት የኾነ ዞን ነው። “ባህላችን ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በተካሄደዉ የሸካቾ ብሄረሰብ የባህል ሲምፖዚየም የተለያዩ ኩነኔቶች…

Read More

“በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ህዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው”፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ህዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው” ሲሉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፤ከደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሲዳማ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። በውይይቱም ተወካዮች በልማት ጉዳዮች ላይ አስተያየቶቻቸውን እና ጥያቄዎቻቸውን ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ግብ ላይ…

Read More

የካራማራ ድል የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ታላቅ ድል ነው

የካራማራ ድል የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ታላቅ ድል መሆኑን የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በመነጠል ታላቋን ሶማሊያ መመስረት በሚል ዚያድ ባሬ በ1969 ዓ.ም መጠነ ሰፊ ወረራ ማድረጉ ይታወቃል። የሶማሊያ ወታደሮች በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬ መሪነት በምሥራቅ ኢትዮጵያ 700 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት ወረራ በፈፀሙ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የጠላትን ሃይል…

Read More

በክልላችን የተገነባው ‘ኢቲ’ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ተገለጸ

በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ‘ኢቲ’ የማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል። የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሙሐመድራፊዕ አባራያ፣ የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብስራት ከበደ እና የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እና የዳውሮ ዞን የስራ ኃላፊዎች የኢቲ የማዕድን ልማት…

Read More

በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት ለቴክኖሎጂ እና አዳዲስ አሰራሮች ትኩረት ተደርጓል – ዶክተር አየለ ተሾመ::

በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት ቴክኖሎጂ እና አዳዲስ አሰራሮችን ማጠናከር ላይ ትኩረት መደረጉን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ተናገሩ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ ላይ ነው። ዶክተር አየለ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በጤና ኤክስቴንሽን፣ በወረዳ ሽግግር እና አጠቃላይ የለውጥ ስራዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል።…

Read More

2 ሺህ የሚሆኑ የቅድመ ወሊድና የወሊድ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እና በሩሲያ የፓን አፍሪካ የመንግስትና የግል አጋርነት የልማት ማዕከል ናቸው የተፈራረሙት፡፡ ስምምነቱ የእናቶችንና የጨቅላ ህፃናትን ህይወት ለማሻሻል የሚረዳ በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ‘ሚድ ዋይፈሪ’ ማዕከል እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡ የሩሲያው የፓን አፍሪካ የመንግስትና የግል አጋርነት የልማት ማዕከል ወደ ሀገር እንዲመጣ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ላበረከተው አስተዋፅኦ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል አስመረቀ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል በዛሬው ዕለት አስመርቋል። አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት ያስመረቀው መሠረተ ልማት በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በልዩ ሁኔታ ለኢኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ የሚገባው መሰረተ-ልማት፤ የአፍሪካን የኢኮሜርስ ኢንደስትሪ ዕድገት ከማፋጠኑም ባሻገር፣ አዲስ አበባን በአፍሪካ ብሎም በዓለም…

Read More

የአድዋ ድል የአብሮነት፣ የአንድነትና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆነ አሰባሳቢ ታሪካችን ነው:- አቶ ቀጀላ መርዳሳ

የአድዋ ድል የአብሮነት፣ የአንድነትና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆነ አሰባሳቢ ታሪካችን ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ተናገሩ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን 128ኛውን የአድዋ በዓልን “አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ አክብሯል። የመታሰቢያ በዓሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ፣ የተቋሙ ሰራተኞችና አባት…

Read More