Getenesh Gebeyehu

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ-ርዕይ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሥራዎችን ሰንዶ ማስቀመጥ የተቻለበት ነው-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ::

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ-ርዕይ ለቀጣይ የዲፕሎማሲ ሥራ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሥራዎችን ሰንዶ ማስቀመጥ የተቻለበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ። አውደ-ርዕዩ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን አስከብራ ለመዝለቅ ያደረገችውን ጉዞ እና ዲፕሎማሲያዊ ከፍታዋን ያሳየ መሆኑንም ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ፤ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ-ርዕይን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።…

Read More

ኢትዮጵያና ኬንያ በቀጣናው ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡ – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኬንያ ጉብኝትን አስመልክቶ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ÷ “ኢትዮጵያና ኬንያ ረጅም ጊዜ የቆየ የትብብር፣ የአጋርነት እና የወንድማማችነት ህብረት አላቸው” ብለዋል፡፡ ቀደምት መሪዎች በሰሩት ስራ በሀገራቱ መካከል ግጭቶች እንደሌሉ በመግለጽ፤…

Read More

ኢትዮጵያና ኬንያ የነበራቸውን የቀደመ ግንኙነት የሚያጠናክር ሥራ እየተሰራ ነው ፡- አምባሳደር ባጫ ደበሌ::

በመንግስት በኩል ኢትዮጵያና ኬንያ የነበራቸውን የቀደመ ግንኙነት የሚያጠናክር ሥራ እየተሰራ ነው ሲሉ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡ ሀገራቱ ረጅም ዕድሜ ያለው ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ግንኙነቱ እስከ ወታደራዊ ውል ድረስ የዘለቀ እንደነበር አንስተዋል፡፡ ወታደራዊ ውሉ ኢትዮጵያ ችግር ሲገጥማት የኬንያ ወታደር ለኢትዮጵያ እስከ መዋጋት እንዲሁም ኬንያ ችግር ሲገጥማት የኢትዮጵያ ወታደር ለኬንያ እስከ መዋጋት የሚደርስ…

Read More

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓድዋ ድልን አስመልክቶ ሀገር አቀፍ ውይይት እያካሄደ ነው::

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ‘‘ዓድዋ የህብረ ብሄራዊነት ድምቀት የአንድነት ውጤት’’ በሚል ሀገር አቀፍ ውይይት እያካሄደ ነው። ውይይቱ 128ኛውን የዓድዋ ድል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ÷ የተለያዩ ፅሁፎችም ቀርበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ዓድዋ የዛሬ 128 ዓመት የተገኘ ድል ብቻ ሳይሆን ለዛሬው ትውልድና ለወደፊቱ ትውልድ ትምህርት የሚሰጥ ነው። የነገዋ…

Read More

28ኛው የአድዋ ድል መታሠቢያ በአልን ለማክበር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደህነት የጋራ ግብረ ሃይሉ የፊታችን የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል በወጣው የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሰላም አዳራሽ ላይ ውይይት አድርጓል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻ ሀላፊ ጀነራል ተስፋዬ አያሌው በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የመላው ኢትዮጵያውያን በዓል የሆነው የአድዋ ድል በአል ሲከበር ምንም…

Read More

በክልሉ የቡና ምርት የግብይትና ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት አለባቸው፦ አቶ ማስረሻ በላቸው::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቡናና ሻይ፣ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን የ2016 ምርት ዘመን የቡና ምርትና ግብይት ጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ ግበረ-ኃይል የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሄደ። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ቡናን በአግባቡ በማምረት ለአለም ገበያ ማቅረብ የሀገሪቱን ጥቅም ማስከበር በመሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ዘርፉን ትኩረት ሰጥተው መምራት እንደሚገባቸው…

Read More

ኢትዮጵያና ኔዘርላንድ በሞጆ ደረቅ ወደብ ቀዝቃዛ መጋዘን ለመገንባት የሚውል 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፋ ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ሄንክ ያን ተፈራርመዋል፡፡ ድጋፍ በሞጆ እየተገነባ ላለው ቀዝቃዛ መጋዘን አዲስ ፖርት ፕሮጀክት ምዕራፍ አንድ የሚውል ነው። በስምምነቱ መሰረት የሚገነባው መጋዘን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሳይበላሹ ለማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡

Read More

”አድዋ የመደመር ተምሳሌታዊ አርማ” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

በፓናል ውይይቱ ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ መኮንኖች፣ የምክር ቤት አባላት፣ አርበኞችና ምሁራን ተገኝተዋል። በኢዜአ አዲሱ ስቲዲዮ እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት የአድዋ ድል የአብሮነትና የአንድነት ተምሳሌት፣ የጥቁር ህዝቦች ነፃነት የነበረው ሚና እንዲሁም የዚህ ዘመን አድዋ ምን መሆን አለበት…

Read More

የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር እና የፍትህ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በሕግ የተሠጣቸውን ተግባራትንና ኃላፊነቶችን መነሻ በማድረግ የጋራ ግቦቻቸውን ለማሳካት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወያይተው ተፈራርመዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በወቅቱ እንዳሉት…

Read More