በህብረተሰቡ ሲነሱ ለነበሩ የልማት ጥያቄዎች መንግሥት የሰጠው ምላሽ የሚደነቅ መሆኑን የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
በዳውሮ ዞን ለረዥም ዓመታት የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረው የወልደሀነ-ዱርጊ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ መጀመር እንዲሁም የታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቀው ለአግልግሎት መብቃቱ እንዳስደሰታቸው ያነጋገርናቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። በዳውሮ ዞን የገና እና የዛባ ወረዳዎች ከአጎራባች የካምባታ እና ጣምባሮ አከባቢዎች ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ጠንካራ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ትስስር እንዳላቸው ያነሱት የአከባቢው ነዋሪ ከሆኑት…
