Getenesh Gebeyehu

የክልሉን የእርሻ ኢንቨስትመንት ወደ 544 በማድረስ 177 ሺህ ሔክታር መሬት እንዲለማ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከፌደራል ግብርና ሚንስትር ጋር በመተባበር በክልሉ በስራ ላይ ከሚገኙ የግብርና ኢንቨስትመንት ባለሀብቶችና ባለድርሻ ጋር የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው። በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የግብርና ግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቀርቦት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስራት አሰፋ: መንግስት ላለፉት የለውጥ ዓመታት የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለማዘመን…

Read More

በመጋቢት እና ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ወራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሳይንሳዊ የምርምር ልህቀት፣ በከተማ ልማት፣ በኢኮኖሚ ሪፎርም እና በቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።

‎• የፕሮጀክቶች ምረቃ እና የሥራ ጅማሮ ‎የመጋቢት ወር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ውስጥ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀዋል። ይህ ማዕከል 40 የላብራቶሪ ክፍሎችን እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮ-ኢኩቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን ያካተተ ነው። ‎በከተማ ልማት ዘርፍ፣ የሚያዝያ ወር በአገልግሎት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ግንባታ ረገድ…

Read More

የክልሉን የንጹህ መጠጥ ዉሃና የሳኒቴሽን ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የውሃ ሽፋን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል-ኢንጂነር በየነ በላቸው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት የዉሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በክልሉ ባሉ ስድስት ዞኖች የአስር ከተሞች የዉሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮጀክት የጥናት ዝርዝር ዲዛይን የመጨረሻ ረቂቅ ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የደቡብ ምዕራብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኮረፖሬሽን በክልሉ የሚስተዋለዉን የንጹህ መጠጥ ዉሃና የሳኒቴሽን ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የጥናትና ዲዛይን ስራዎችን ከክልሉ ዉሃ፣ማዕድንና…

Read More

ባለፉት ስምንት የለውጥ አመታት በከተማቸው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን በሚዛን አማን ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ነጋዴዎች ተናገሩ

“ለሁለንተናዊ ብልጽግና የማህበረሰቡ ሚና” በሚል ሀሳብ ከሚዛን አማን ከተማ ንግድ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በውይይት መድረኩ የተሳተፉና በተለያዩ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች፤ በከተማዋ በተለይም ለውጡ ከመጣ በኋላ በርካታ የልማት ስኬቶች መመዝገባቸውን እና ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን ነው የተናገሩት። በተለይም በከተማዋ የአየር መንገድ ግንባታው፣ የደንቢ ሎጅ እና የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን እድገት እያፋጠነው መሆኑን አመላክተዋል። በከተማዋ…

Read More

በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የታርጫ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በመሆኑ መደሰታቸውን የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በበኩላቸው መናኸሪያው ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ንብረት ውጭ በሚያድርበት ወቅት ካለው ስጋት ነፃ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች አቶ ወ/ማርያም ብትሬ እና ወ/ሮ አባይነሽ ሳና ቀደም ሲል የታርጫ ከተማ መናኸራያ የመንገደኞች ማረፍያ፣ ካፍቴሪያ፣ የትኬት መቁረጫ ቢሮና መኪና ማቆሚያ ቦታ ምቹ ያለመሆኑን አንስተው አሁን ግን ዘመናዊ መናኸሪያ ተገንቢቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። በግንባታ ምክንያት…

Read More

የክልሉ መንግስት የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችሉ የልማት ስራዎችን በትኩረት ይሰራል፦ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

በምረቃ ስነስርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የለውጡ መንግስት በርካታ የተወዛዘፉ የቤት ስራዎችን ተቀብሎ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው ዛሬ የተመረቀው የታርጫ ህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። የመነኸሪያ ያለመኖር ለዜጎች ለስምርት ምቹነት፤ የተሸከርካሪ ብቃት ለማረጋገጥ ፣ ተሳፋሪውን ተገቢውን ታርፍ ለማስከፈል ማነቆ ከመሆኑም ባሻገር ህዝብን ለእንግልት እያዳረገ መቆየቱን ተናግረው፤ አሁን የግንባታው መጠናቀቅ…

Read More

የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማዳመጥና ምላሽ በመሰጠት እየተሰሩ ያሉት ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል :- አቶ ፍቅሬ አማን

በከተሞች የህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለማዳመጥና ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚያስችል የህዝብ ውይይት መድረክን አስመልክቶ ክልላዊ የዘርፍ አመራሮች ውይይት መድረክ የክልል የሚመለከታቸው ተቋማት አመራሮችና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ባለፉት ዓመታት ከከተማ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉት ህዝባዊ የውይይት መድኮች የተነሱትን መሰረታዊ የልማትና…

Read More

መንግስት የዜጎችን ህይወት ትርጉም ባለው ሁኔታ በሚቀይሩ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ፦ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የተገነባውን የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከልና በወረዳው የተገነባውን የአስተዳደር ህንፃ መርቀው ከፍተዋል። በማሪ ማንሳ ወረዳ ማሪ ከተማ የተገነባው የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከል በአካባቢው ካለው የእንስሳት ዕምቅ ሀብት የሚመነጨውን ኢኮኖሚ በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። አካባቢው በእንስሳት ሀብት፣ በእርሻና…

Read More

ተጠናቅቆ ለአገልግሎት የበቁና ቀጣይ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች የብልጽግና ፓርቲ ለህዝብ ጥያቄ የሰጠዉ ምላሽ ማሳያ ናቸዉ፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የህዝብን የልማት ጥያቄ በተገቢው መንገድ ለመመለስ በክልሉ መንግስት የተጀመሩ የተለያዩ ልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን የገለጹት በዳውሮ ዞን ኢሳራ ባሌ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ባኖሩበትና ግንባታው የተጠናቀቀውን የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። ባለፉት ዓመታት የተሰጡ የቤት ስራዎች ተጠናቅቆ እየተመረቁ መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀመሩ…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ግንባታና የአፍሪካ አቪየሽን ልህቀት ተምሳሌት ነው – ከፍተኛ አመራሮች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ግንባታ ጉልህ ሚናው ብሔራዊ ኩራትን ከመፍጠር ባለፈ የአፍሪካ አቪየሽን የልህቀት ተምሳሌት ነው አሉ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በማስመልከት ከደንበኞችና አጋሮች ጋር የደንበኞች ተሞክሮ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመርሐ ግብሩ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው…

Read More