ባለፉት 8 የለውጥ አመታት የተመዘገቡ ድሎችን የሚዘከር፤ ለቀጣይ ጉዞ አንድነትን ሚያጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅሰቀሳ በሸኮ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች እየተካሄደ ነው
የሰልፉ ተሳታፊዎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአገር፣በክልሉ፣በዞኑና በወረዳው በተለያዩ ዘርፎች የመተመዘገቡ ድሎችን በማንሳት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አጋርነታቸውን አሳይተዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሪ ጉርሙ በግዝመሬት ክላስተር በተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ፤አገርን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያሻግሩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። በአገር ደረጃ ከተመዘገቡ ድሎች ባሻገር በዞኑ ብሎም በአካባቢው የተመዘገቡ ውጤቶችን ጠቅሰው…
