የኪነጥበብ ሥራዎችን በማበረታታት ለሀገር መንግሥት ግንባታ የሚያበረታቱ አስተዋጽኦ ማጉላት እንደሚገባ ተገለጸ።
በሰዓሊ አብረሃም ተስፋዬ የተዘጋጁና የካፋን ነገሥታት ታሪክ፣ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓትና የማኅበረሰቡን ጥንታዊ አኗኗር የሚዘክሩ የስዕል አውደርእይ በቦንጋ ከተማ ተከፍቷል። የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን አሰናስነው የሚይዙ በመሆናቸው ለማኅበረሰብ የታሪክ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ነው በአውደርዕይ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የገለጹት። ኪነ-ጥበብ የአንድን ማኅበረሰብ ቱባ ባህል፣ ዕሴት እንዲሁም…
