BLOGS
ተናፋቂው “ማሽቃሮ” በካፋ ንጉሳዊ ስርዓት ታጅበው በድምቀት መከበር ጀምሯል።
የካፈቾ ብሔር ቱባ ባህላዊና ታሪካዊ ዕሴት ያለውና እነዚህንም የማህበረሰቡ ተውፊቶች ጠብቆ ማቆየት የቻለ ማኅበረሰብ ነው። ከእነዚህ የብሔሩ ባህላዊ ሀብቶችና ክዋኔዎች መካከል አንዱ ደግሞ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው የዘመን መለወጫ በዓል የኾነው (ማሽቃሮ) ነው፡፡ ማሽቃሮ በየዓመቱ መስከረም አጋማሽ የብሄረሰቡ ተወላጆች እና ወዳጆች ተስብስበው የነገስታት መናገሻ በኾነውና ከቦንጋ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው “ቦንጌ ሻምበቶ” በጋራ የሚያከብሩት በዓል ነው።…
ካፈቾ ዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በነግስታት መናገሻ ቦንግ ሻንበቶ በተለያዩ ትይንቶች መከበር ጀምሯል
ታላቁን ማሽቃሮ ለማክበር ታዳሚዎች ከሁሉም አቅጣጫ ወደ ቦንግ ሻንበቶ እየተመሙ ነው። “ማሽቃሮ” በተለያዩ ትርዕቶች ከወዲሁ እየደመቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል። በአሻግሬ ገ/ወልድ
ጥንታዊው የማህበረሰብ አስተዳደር ስርዓትና “ማሽቃሮ” በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ ተጠየቀ
ለዘመናት ተጠብቆ ለዓለም የበቃውና በዩኔስኮ የተመዘገበው የካፋ ባዮስፌር ሪዘርቭ የህልውናው መሰረት፣ የካፊቾ ህዝብ ጥንታዊ የአስተዳደር ስርዓት የሆነው “ምክረቾ” መሆኑ ተገለጸ። በመሆኑም ይህ ድንቅ ባህላዊ ስርዓትና መገለጫው የሆነው የማሽቃሮ በዓል፣ ተገቢውን ዓለም አቀፍ እውቅና በማግኘት በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ሊመዘገብ እንደሚገባው ባለሙያዎችና አመራሮች አሳሰቡ። ይህ የተገለጸው የማሽቃሮ በዓልንና የካፋ ባዮስፌርን 15ኛ ዓመት ምሥረታን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የፓናል…
አቶ ታምሩ ቦኒ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት፣ አቶ ታምሩ ቦኒን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሾሟል። አቶ ታምሩ ከዚህ ሹመት በፊት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሹመቱ የተከናወነው የዞኑ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሲሆን፣ የቀድሞው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ጌታቸው…
“ማሽቃሮ ቆጥረን የማንጨርሰው ትውፊቶችን የያዘ የካፋ ማንነት መገለጫ በዓል ነው “-አቶ ማስረሻ በላቸው
የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በዓል፣ ከባህላዊ ክዋኔው ባሻገር ለዘመናት የዘለቀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስርዓትንም የያዘ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ። አቶ ማስረሻ ይህን የተናገሩ የብሔሩ ተወላጆች የፌደራል ተቋማት ኃላፊዎች፣ የዩኔስኮ ተወካዮች፣ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የማሽቃሮ በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀ የፓናል ውይይት ላይ…
ማሽቃሮ ለሠላምና ለአብሮነት በሚል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነዉ
የካፌቾ ብሔር ዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በዓል አከባበር አካል የሆነው ፓናል ውይይት ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ የብሔሩ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል ። ውይይቱ የካፌቾ ብሔር ቱባ ባህል ልማቶች ላይ ትኩረት አድርጎ በምክሬቾ፣ በተለያዩ የመንግስት ኃላፊዎች እና ባለድርሻዎች ይመክሩበታል። በአሻግሬ ገ/ወልድ
የዘንድሮው የማሽቃሮ በዓል በታላላቅ ሀገራዊና ታሪካዊ ክስተቶች ታጅቦ በድርብ ደስታ ይከበራል – አቶ ፍቅሬ አማን
የህዳሴው ግድብ ምርቃትና የካፋው ንጉስ የታቶ ጋኪ ሻሬቾ ዘውድ መመለስ ለበዓሉ ልዩ ድምቀት ሰጥተውታል ስሉ አቶ ፍቅሬ አማን ገልጸዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፣ ለካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ ‘ማሽቃሮ’ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኃላፊው በመልዕክታቸው ፣ የዘንድሮው በዓል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በታላቅ ስኬት መመረቅና የካፋ…
በሀገሩ ባይተዋር ሆኖ ዝናው በዓለም የናኘው ኢትዮጵያዊው ጌሻ ቡና
ኢትዮጵያ ስለምታመርተው፣ ነገር ግን በቅጡ ገቢ ስለማታገኝበት ጎሪ ጌሻ, ጌሻ ቡና ምን ያህል ያውቃሉ? ጌሻ ቡና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን በጎሪ ጌሻ ወረዳ አካባቢ ይበቅላል። ጌሻ ቡና ጠቀም ያለ የውጭ ምንዛሬ የማስገኘት አቅም ቢኖረውም፤ በተበታተነ ሁኔታ ስለሚመረት በጥቂት ምርት ብቻ ተወስኗል ይላሉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ አካላት። አጥኚዎቹ እንደሚሉት፥ ጌሻ ቡና በፈረንጆቹ…
የማሽቃሮ በዓል የይቅርታ፣ የፍቅርና የማህበራዊ ትስስር ተምሳሌት ነው – ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው “ማሽቃሮ” የይቅርታ፣ የፍቅርና የማህበራዊ ትስስር ተምሳሌት መሆኑን ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዓሉን አስመልክተው ለመላው የካፌቾ፣የናኢና የጻራ ብሔር ተወላጆች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ ማሽቃሮ ከቀን መቁጠሪያነት የዘለለ ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ፋይዳ ያለው የማንነት መገለጫ በዓል መሆኑን አስምረውበታል። ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ…
