ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለክልሉ ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ማቅረባቸውን ቀጥለዋል ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት ሪፖርት በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ው ጤታማ መሆናቸውን አብራርርዋል ፡፡በዚህም ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፡- በዋና ዋና የአዝርዕት ሰብሎች በመኸር፣ በበጋ መስኖ እና በበልግ ወቅት 745,090.5 ሄ/ር ማሳ በዘር ተሸፍኗል፡፡ በበጀት ዓመቱ 20 ሚሊየን 632 ሺህ 359 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል፡፡ በበጋ መስኖ ስንዴ 5,017 ሄ/ር መሬት በዘር በመሸፈን 149 ሺህ106 ኩንታል…
