የክልሉ ሚዲያ ኔትወርክ ከተቋቋመ ወዲህ የተከናወኑ ተግባራትን የአፈጻጸም ሪፖርት ምክርቤቱ አድምጧል።
የተቋሙን ሪፖርት ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መንግስቱ መኩሪያ ለምክርቤቱ አቅርበዋል። ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት ሚዲያ ኔትወርኩ በማህበራዊ የሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ተቋሙ የክልሉን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በተዘረጉ የማሰራጫ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል ። ሚዲያው በተሟላ አቅሙ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ተቋሙን በሰው ኃይልና በቁሳቁስ ለማሟላት ጥረቶች መደረጋቸውን አቶ…
