የሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲካሻ ቤንጊ”በቴፒ ማዕከል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ነው
ሸካ ዞን፤ ጥር 14/2018 (መ.ኮ.ጉ)የሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል የሆነው “ቲካሻ ቤንጊ”በሸካ ዞን ቴፒ ማዕከል በተለያዩ ማራኪ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ በደመቀ ሁኔታ መከበር ጀምሯል። “ቲካሻ ቤንጊ”ይቅርታና መተማመን የሚሰፍንበት፣ ግጭቶች በሽምግልና የሚፈቱበትና የአብሮነትና የሰላም እሴት ጎልቶ የሚገለጥበት የብሄረሰቡ ቱባ ባህል ነው። “ቲካሻ ቤንጊ”ከአዝመራ መሰብሰብ በኋላ የሚከበር ታላቅ በዓል ሲሆን አሮጌውን ዘመን ተሸኝቶ አዲሱን ዓመት በተስፋ፣…
