ወንጀለኞችን ተጠያቂ ከማድረግ ባለፈ በሙስና ወንጀል የተመዘበረ ሀብትን ማስመለስ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቤተልሔም ዳንኤል ተናገሩ
የክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ኦዲት ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት በቦንጋ ከተማ እያደረጉ ነው። የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቤተልሔም ዳንኤል የሙስና ወንጀል የህዝብንና የመንግስትን ኃላፊነት ባልተገባ መልኩ በመጠቀም የሚፈጸም በመሆኑ ውስብስብና ለምርመራ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቀ የመጣ በመሆኑ የመከላከሉና ወንጀለኞችን ተጠያቂ የማድረጉ ስራን ተቋማት…
