Trendings

በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ሰባተኛው ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነሥርዓት ተካሂዷል።

በ2010 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ይኽ ሥነሥርዓት የዜግነት የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት የሚፈፅሙ ዜጎችን ለማበረታታት ታቅዶ የሚተገበር ነው። በዘንድሮው መርሃ ግብር 700 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በ2017 ዓመተ ምህረት እንደነበራቸው አስተዋጽኦ መጠን 105 የፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 የወርቅ ደረጃ፣ 350 ደግሞ የብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል። የጋራ አስተዋጽኦዋቸው በሥራ ዘመኑ 900.22 ቢሊዮን ብር በግብር…

Read More

የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ ተግባራት ትኩረት ተሰቷቸዋል-አቶ አገኘሁ ተሻገር

የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ ተግባራት ትኩረት እንደተሰጣቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ የመንግስታት ግንኙነት፣ ዴሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ-መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የሕገ መንግስትና የፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምን በማዳመጥ የ2018 ዓ.ም…

Read More

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 የትምህርት ዘመን ሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ አደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል። 1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1…

Read More

ምክር ቤቱ 13 አቤቱታዎች የሕገመንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ሲል ውሳኔ አሳለፈ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከቀረቡለት አቤቱታዎች ውስጥ 13ቱ የሕገመንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ሲል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል። በጉባኤው የሕገመንግሥት ትርጉምና የውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ መርምሮ ባቀረባቸው የውሳኔ ሃሳቦች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም በምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል…

Read More

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ዕድል የመጀመሪያውን ምርቷን ወደተለያዩ ሀገራት ልትልክ ነው – የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ድርድርን ማጠናቀቋን ተከትሎ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሸቀጦች ዘርፍ የንግድ ትግበራዋን በይፋ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ እንደገለጹት ፤ የመጀመርያው የንግድ ልውውጥ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ አገራት ላይ ትኩረት ያደርጋል። ነፃ ንግድ ቀጣና ንግድ ማስጀመሪያው ላይ በኢትዮጵያ አየር…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የPulse of Africa ሚዲያ ሥራ መጀመር አፍሪካን በአሉታዊ ገጽታ የማቅረብ ሥራን ለመመከት ብሎም የራሳችንን ትርክት በራሳችን የመቅረጽ ተግባራችንን የምናፀናበት ጠቃሚ ርምጃ ነው። ምንም እንኳ አፍሪካ ሰፊ እና እምቅ ሀብት ያላት አኅጉር ብትሆንም አብዛኛውን ጊዜ እንደ አነስተኛ እና አቅመቢስ ተደርጋ ትሳላለች። በዚህ የተነሳ ነው አነስተኛ ግን እጅግ ትርጉም ያለው የPulse of Africa ጅማሮ በመጪዎቹ ጊዜያት ከፍ…

Read More

የደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በባቱ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የምስረታ በዓል ላይ የኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል። በተጨማሪም የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል…

Read More

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመረ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመሯል፡፡ ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ቃለጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ የቀጠለ ሲሆን በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል።

Read More

መንግስት በማህበራዊ ዘርፍ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፦ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

መንግስት በማህበራዊ ዘርፍ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፦ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መንግስት በማህበራዊ ዘርፍ በተለይም በጤና፣ ትምህርትና ስፖርት ዘርፎች ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስታወቁ፡፡ ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ተካሄዷል። በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መንግስት ባለፈው…

Read More