በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል ምርት ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷ መንግስት ዘርፉን ለማዘመን ባከናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡ በዚሁም የመስኖ ልማትን ለማጠናከር በበጀት ዓመቱ ከስድስት በላይ ከፍተኛ ግድቦች እንዲሁም ከ145 ኪሎ ሜትር በላይ ካናሎች ተገንብተው ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የበጋ መስኖ ልማትን የሚያግዙ ከ100 በላይ አነስተኛ…
