የመሃሉ ዘመን ወጥመድን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጡት ማብራሪያ
የመሃል ዘመን ማለት በሽግግሩ ማጠናቀቂያና በጸናው ስርዓት መጀመሪያ ላይ ማለት ነው። ስድስት ዓመታት የፖለቲካ ሪፎርም አደረግን የሰፈር ፓርቲ አጥፍተን ብልጽግናን ፈጠርን፣ በየሰፈሩ የነበረን ፓርቲ አምጥተን ብልጽግናን መፍጠር በራሱ ትልቅ እምርታ ነው። እኛ ያደረግነውን እኮ ብዙዎቹ አልቻሉም ገና በማህበራዊ ድረ ገጽ ውስጥ ነው ያሉት። ከተቋማት ሪፎርም ጀምሮ የተሟላ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስላደረግን ነው መሃል ያልነው። ይሄ ማለት…
