Trendings

የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው።

ከሀምሌ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ይገኛል። በዕለቱ የፓርቲ ሰነዶችና መመሪያዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው። የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። #prosperity

Read More

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች ኢትዮጵያን የሚመጥን ዘመናዊ አሰራር መገንባቱን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከክልል መዝጋቢ እና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያተኮረ ጉባኤ እያካሄደ ነው። በመድረኩ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፣ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት እንዲሁም ሌሎች…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፤ የዋና ጽ/ቤትና የክልልና የከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤቶች አመራሮች ተገኝተዋል። በመርሀግብሩ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት መሪ ዕቅድ ሪፖርት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። #prosperity

Read More

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጫካ ፕሮጀክት ችግኝ ተከሉ

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዛሬው ዕለት በጫካ ፕሮጀክት በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ታዬ በዛሬው ዕለት ያከናወኑት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሠራተኞች እና አመራሮች ጋር በመሆን ነው፡፡ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሀሳብ የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ሲሆን፤ በመላ ኢትዮጵያ ችግኝ እየተተከለ ይገኛል። #FM

Read More

በአንድራቻ ወረዳ የጌጫ ከተማ የህዝብ መድኃኒት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ብቁ ሆኗል።

የህዝብ መድኃኒት ቤቱን የክልሉ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ መርቀዋል። በምረቃው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወሰን ጨመሰ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚቀርብበት ነው ብለዋል። በመንግሥት ተቋማት የማይገኙ መድኃኒቶች በአማራጭነት ቀርበው ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ያግዛልም ብለዋል። ለአገልግሎት በበቃው የህዝብ መድኃኒት ቤት የሰው ሀይል ቅጥር ለማሟላት ትኩረት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል።…

Read More

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ጋር በማስተሳሰር በስፋት እየተከናወነ ነው

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ጋር በማስተሳሰር በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሃይ ጳውሎስ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በየካ ተራራ በመገኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አመራር አባላት እና ሰራተኞች ጋር የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም ቀደም ብሎ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሪዮ ዴጄኔሮ ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና በማንኛውም ሁኔታ የማይለያዩ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋሮች መሆናቸውን እንደተናገሩ ሺንዋ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኮሙኒኬሽን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በቱሪዝምና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባለብዙ ወገን ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዲያድግ ለማድረግ የሚያስችል…

Read More

“ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለምአቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ የሰላም፣ የጸጥታ እና ዓለምአቀፍ አመራር መድረክ መክፈቻ ላይ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ስኬታማ ትብብርን ለማስቻል አፀፋዊ መተማመንን የሚያሳድጉ ዓለምአቀፍ ተቋማት የመኖርን አጣዳፊነት አንስተዋል። ዓለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት ይረዳ ዘንድ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅራቸው ምሉዕነት ባለው መልክ የሚሻሻልበትን ሁኔታም…

Read More

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ48ኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለሁለተኛው ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የእድገት ልማት ፖሊሲ ማስፈፀሚያ የሚውል 258,100,000 ኤስ.ዲ.አር እና ለፍጥነት መንገድ ልማት ድጋፍ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 27,300,000.00 ኤስ.ዲ.አር የፋይናንስ ድጋፍ እና የብድር ስምምነቶችን ለማጽደቅ በቀረቡ ሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ሁለቱም ብድሮች ከወለድ ነጻ፣ 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው ሆኖ የ6…

Read More

ለሕብረተሰብ ጥቅም በሚሰሩ የልማት ስራዎች ሁሉም ትብብር ሊያደርግ ይገባል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። ለማህበረሰብ ጥቅም ከሚሰሩ ልማቶች በተጨማሪ የኢንቨስትመንት የልማት ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸው፤ እንደ ቴሌ ኮሙኒኬሽን፣ መብራት ኃይል፣ አየር መንገድ፣ የልማት ስራ በሚሰሩበት ወቅት 100 በመቶ ካሳ ይከፍላሉ ብለዋል። ነገር ግን ካሳ የሚጠየቅበት መንገድ ለምን ዓላማ? የሚለውን በደንብ ማለየት…

Read More