በግብርናው ዘርፍ የስርዓተ-ጾታ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መዋቅራዊ ለዉጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ስርዓተ-ፆታና ኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪምንግ ጋር በመተባበር ለክልሉ ግብርና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፤መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶችና ፕሮግራሞች በስርዓተ-ፆታና ማህበራዊ ጉዳይ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማስፋት የሚያስችል የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የግብርና ልማት ዕቅድ ጀንደር ስትራቴጂ ሰነድ በግብርና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ…
