በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓል እየተከበረ ነው
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉም የሃይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮች ምዕምናንና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። በዓሉ በቅዳሴ፣ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና በሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል። በዓሉ በመላው ሀገሪቱ ባሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከብሮ እንደሚውልም ተገልጿል ሲል ደሬቴድ ዘግቧል።
