የጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የሩዋንዳ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው: – ቢልለኔ ስዩም

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሩዋንዳ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ፡፡ ቢልለኔ ስዩም የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸውን የሩዋንዳ ኪጋሊ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም ፥ ጉብኝቱ በሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አንደኛው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፖል…

Read More

እስካሁን የተደረጉ የባህል ስፖርቶችና ባህል ፌስቲቫል ውድድሮች ውጤት ተገለጸ::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ የሚካሄደው 21ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 17ኛው የባህል ፌስቲቫል ውድድር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ባህል ስፖርቶች ውድድርና ባህል ፌስትቫል ቡብ፥ ገበጣ 12 ጉድጓድ የወንዶችና የሴቶች፣ሻህ የወንዶችና የሴቶች፣ ኮርቦ የሴቶች ፍፃሜ እና ሌሎች ባህላዊ የስፖርት ውድድሮችና ባህል ፌስቲቫሎች በሁለቱም ፆታዎች ተካሂደዋል።…

Read More

ለበልግ ወቅት የሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ መቅረቡ ተገለጸ::

ለበልግ እርሻ ልማት 469 ሺህ 80 ነጥብ 84 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ መቻሉን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ለ2016/17 የምርት ዘመን 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚገዛና ከዚህ ውስጥ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ 11 ነጥብ 19 ሚሊየን ደግሞ ኤን ፒ ኤስ ማዳበሪያ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ የ2016/17 ምርት የአፈር…

Read More

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በቦንጋ ከተማ ስልጠና መስጠት ጀመረ::

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በልዩ ሁኔታ ለተመረጡ ኢንተርፕራይዞችና ባለሀብቶች ለ 5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና በቦንጋ ከተማ መስጠት ጀምሯል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አበራ በዙም ባስተላለፉት መልዕክት የአሁኑ ስልጠና ከዚህ ቀደም ከነበረው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና የተለየ መሆኑን ተናግረዋል ። ለዚህ…

Read More

አዲስ አበባን የትስስርና ብሔራዊ ትርክት የተረጋገጠባት ከተማ ለማድረግ እየተሰራ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባን የትስስር እና ብሔራዊ ትርክት የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የአባላት ኮንፈረንስ “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና “በሚል መሪ ሃሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ የተገኙት አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት ÷ የብልጽግና ፓርቲ በግማሽ ምርጫ ዘመን አፈጻጸሙ በተለያዩ ዘርፎች…

Read More

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ጀነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ::

የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በተለያዩ አጭር የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ጀነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ኖጎ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እና ጥሪ…

Read More

ብልጽግና ፓርቲ በሁለት አመት ከግማሽ በሁሉም ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት በማስቀጠል የነበሩ ጉድለቶችን በማረም አባሉና አመራሩ በቀጣይ ይበልጥ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ተባለ

በሸካ ዞን በሁሉም ከተማና ወረዳ አስተዳደሮች ሲደረገ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ አባላት ዞናዊ የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተጠናቋል። “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ፓርቲው በግማሽ የምርጫ ዘመን ያከናወናቸውን ተግባራት በማጠናከር ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ ጊዜያት አባላቱና አመራሩ ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ ተጠይቋል። የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ በመድረኩ እንደገለጹት ፓርቲው በምርጫ ወቅት ለህዝብ…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል አስመረቀ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ55 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል በዛሬው ዕለት አስመርቋል። አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት ያስመረቀው መሠረተ ልማት በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በልዩ ሁኔታ ለኢኮሜርስ ሸቀጦች እንዲሁም ለፖስታ እና ጥቅል መልእክቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ወደ ስራ የሚገባው መሰረተ-ልማት፤ የአፍሪካን የኢኮሜርስ ኢንደስትሪ ዕድገት ከማፋጠኑም ባሻገር፣ አዲስ አበባን በአፍሪካ ብሎም በዓለም…

Read More

ኢትዮጵያና ኔዘርላንድ በሞጆ ደረቅ ወደብ ቀዝቃዛ መጋዘን ለመገንባት የሚውል 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፋ ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ሄንክ ያን ተፈራርመዋል፡፡ ድጋፍ በሞጆ እየተገነባ ላለው ቀዝቃዛ መጋዘን አዲስ ፖርት ፕሮጀክት ምዕራፍ አንድ የሚውል ነው። በስምምነቱ መሰረት የሚገነባው መጋዘን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሳይበላሹ ለማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡

Read More

”አድዋ የመደመር ተምሳሌታዊ አርማ” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

በፓናል ውይይቱ ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ መኮንኖች፣ የምክር ቤት አባላት፣ አርበኞችና ምሁራን ተገኝተዋል። በኢዜአ አዲሱ ስቲዲዮ እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት የአድዋ ድል የአብሮነትና የአንድነት ተምሳሌት፣ የጥቁር ህዝቦች ነፃነት የነበረው ሚና እንዲሁም የዚህ ዘመን አድዋ ምን መሆን አለበት…

Read More