Trendings

ኢትዮጵያ ዐዲሲቷ የተስፋ ዓድማስ ናት!

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የታሪክ አውድ ውስጥ አዲስ ትርጉምና ጽኑ ቃል-ኪዳን ተላብሶ ብቅ ያለ፣ ለሀገራችንና ለሕዝቦቿም አዲስ የተስፋ አድማስን የፈነጠቀ ክስተት ነበር። ይህ ዕለት ኢትዮጵያን ተብትቦ ይዞ ከነበረው ውስብስብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቅርቃር አውጥቶ ወደ ብሩህ መጻኢ ዕድል ለማሸጋገር የተገባ ታላቅ የትውልድ ውል ሆኖ ተመዝግቧል። ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2018…

Read More

ከዕዳ ጥገኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት

ኢትዮጵያ ከአሳሪውና ከአባካኙ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሥርዓት ወጥታ፣ በዕውቀትና በዲሲፕሊን የሚመራ ጠንካራ የኢኮኖሚ መዋቅር መገንባት ችላለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገራዊ ጸጋዎችን ወደ ላቀ ምርታማነት ለመቀየርና የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የጀመራቸው ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎች፣ ዛሬ ላይ ሀገራችንን በዓለም ፈጣን ዕድገት ካላቸው አሥር ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርገዋታል። አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተለያዩ ውስብስብ ሀገራዊና…

Read More

በክልሉ የትምህርት ምዘና እና የፈተና አስተዳደር ሥርዓትን ለማዘመን እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ውጤቶች እየተመዘገቡ ናቸው- አቶ አልማው ዘዉዴ

”የዘመነ የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም ሀገራዊና ክልላዊ የፈተና አስተዳደር የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩን ያስጀመሩት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘዉዴ እንዳሉት፤ በትምህርት ሴክተር ሪፎርም ከተደረጉ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የፈተና ምዘና እና የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ማዘመን…

Read More

የሥራና ክህሎት ቢሮ ”ብሩህ አዕምሮዎች፤በክህሎት የበቁ ዜጎች በሚል መሪ ቃል የክህሎት፤ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነዉ።

በውድድርና ኤግዚቢሽን መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ እንደገለጹት፤ በፊት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚሰጠዉ ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ በዘርፉ ውጤት ተገቢዉ ዉጤት ሳይመዘገብ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም የተጀመሩ የተቋማት ግንባታዎች ተጠናቅቀዉ አገልግሎት ባለመስጠታቸውና ተቋማት በሚፈልገው ልክ ቴክኖሎጂ ከማሸጋገር አንጻር የነበራቸው ውስንነቶች ተግዳሮት እንደነበርም አስታውሰዋል። ዋና አፈ-ጉባኤው…

Read More

የግብርና ኤክስቴንሽን የምክር አገልግሎትን ፈጣን ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም (Pact Programme) ለአርሶ አደር መስክ ትምህርት ቤት አመቻቾች ስልጠና በሚዛን አማን እየተካሄደ ይገኛል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ተስፋዬ እንደተናገሩት ፕሮግራሙ በክልሉ በሴፍትኔት በታቀፉ ዞኖችና ወረዳዎች ላይ የሚሰራ መሆኑን ገልጸው በዚህም በምዕራብ ኦሞ ዞን…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በወጣትነት ዘመናቸው ሰላም አስከባሪ በመሆን ጭምር ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል፡ – ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በወጣትነት ዘመናቸው ሰላም አስከባሪ በመሆን ጭምር ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል ሲሉ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሩዋንዳውያን የ”ኪዊቡካ 30″ ዓመት መታሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል፡፡ መርሃ ግብሩ በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ 30ኛ ዓመት የሚያስብ ነው፡፡ በመርሃ ግበሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ሩዋንዳን በወቅቱ ከገጠማት…

Read More

የኮሪደር ልማት ከ60 በመቶ በላይ ሀብታችንን ጥቅም ላይ እንድናውል ያስችለናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያን ከተሞች ለማነቃነቅ ያለመ ሥራ እንደሆነ ገልጸዋል። ከተሞች 60 በመቶ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) መያዛቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከተማ ከተዘነጋ ይህን ያህል ሀብት ጥቅም ላይ እንደማይውል ተናግረዋል። ከ50 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለው በአዲስ አበባ እንደሆነም አውስተው፣ አዲስ አበባ…

Read More

በ2016 በጀት ዓመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋግጡ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል። ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከምክርቤቱ አባላት ለተነሱላቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበና ጉባኤ በሁለተኛው ቀን ውሎ በተነሱ የአስፈጻሚ ተቋማት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከምክርቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት…

Read More

በሰሜን ቤንች ወረዳ የባህር ዛፍን በማንሳት በምትኩ በፍራፍሬና በሰብል ለመሸፈን እየተሰራ ያለው ሥራ ተሞክሮ የሚቀመርበት ተግባር ነው፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች የ2017 ዓ/ም ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ማስጀመሪያ ጎን ለጎን በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ከእርሻ ቦታ ባህርዛፍን በማንሳት በፍራፍሬና ሰብል የተሸፈነውን ማሳ የመስክ ምልከታ ተደርጓል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በእርሻ ቦታ ላይ ያለውን ባህርዛፍ በማንሳት በፍራፍሬና በሰብል…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከዳውሮ ዞን ከተወጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ::

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ እየተከናወነ ባለውና በቀጣይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ነው ውይይት ያደረጉ። መንግስት ከሚሰራው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን መላው የዞኑን ህዝብ በማስተባበር የዞኑን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልሰራ እንደሚገባም አንስተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ባለሀብቶችን በማስተባበርና ኢንቨስትመንትን በመጋበዝ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ትልቁ ተግባር ልሆን ይገባልም ብለዋል። በዞኑ ባለፉት አራትና አምስት የለውጥ አመታት በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ…

Read More