Trendings

Getenesh Gebeyehu

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና በሚዛን-ቴፒና ቦንጋ የዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝደንቶች፣ ምክትል ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ተጀምሯል።

የሁለተኛው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተፈታኞች ፈተናቸውን በእንግሊዝኛ ትምህርት ዓይነት መጀመራቸውን ከዩኒቨርሲቲዎቹ መረጃ መወቅ ተችሏል። የሁለቱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች ባስተላለፉት መልዕክት ለተማሪዎች መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ፈተናውን ተረጋግተው መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ፈተናው ከዛሬ ጀምረው ሶስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛውም ዙር የፈተና አሰጣጡ በወረቀት እና በበይነ-መረብ /Online/ እንደሚሰጥ ታውቋል። በአሻግሬ ገ/ወልድ

Read More

ለሀገራችን ልማትና ዕድገት የሚረዳ ተዓማኒነት ያለዉ መረጃ ለማደራጀት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሚና ከፍተኛ ነው፦ አቶ በላይ ተሰማ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ዘርፍ ከክልል ቢሮ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት የጋራ ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት፤የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንደተናገሩት፤ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ እና አስተዳደራዊ ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ…

Read More

የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማስመረቅ ሸካ ዞን፣ ቴፒ ከተማ ገቡ

የሥራ ኃላፊዎቹ በሸካ ዞን በሚኖራቸው ቆይታ የቴፒ አየር ማረፊያ ዳግም ሥራ የማስጀመር እና የቴፒ የቡና ቅምሻ ማዕከል ይፋዊ ስራ የሚያስጀምሩ ይሆናል። በኢፌዲሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ፤ ቴፒ ከተማ ሲደርሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ…

Read More

በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 636 አዳዲስ ቤቶች ይገነባሉ:-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው አማካኝነት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የሚገነባውን የአረጋውያን ቤት ግንባታ አስጀምረዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብ በክረምት በጎ ተግባር ላይ የጉልበት የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። የክረምት ወራት በጎ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየተለመደ የመጣ ባህል መኾኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ካለው ላይ በማካፈል እንዲሁም ደጋፊ…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የአያሌው ህይወቴ የወተት ላሞች እርባታ ጎበኙ

አቶ አያሌው የወተት ምርታማነትን ለማሻሻል የተሟላ ፓኬጅ በመጠቀም እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል ። አቶ አያሌው ካላቸው 16 ላሞች በቀን 80 ሊትር ወተት ለህብረተሰቡ እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል። በአማካይ ከአንድ ላም በቀን 15 ሊትር ወተት እንደሚገኙ ገልጸዋል። በጉብኝቱም የተጀመረው ስራ የሚበረታታ መሆኑንና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ። ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ምክትል ርዕሰ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያን ወደ ፈጣን ዕድገት እየመሯት ስለሆነ ሊመሰገኑ ይገባል፡- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ ወደ ፈጣን ዕድገት እየመሯት ስለሆነ ሊመሰገኑ ይገባል ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ሊቀመንበሩ፤ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያመጣች ያለው ለውጥ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ሕዝብ ብዛት…

Read More

በበጀት ዓመት ከ30ሺህ ለሚበልጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች አግልግሎት መስጠቱን የቴፒ ከተማ የህዝብ መድኃኒት ቤት አስታወቀ።

በህዝብና በከተማ አስተዳደሩ ትብብር በ2015 ተቋቁሞ ወደ አግልግሎት የገባው የቴፒ ከተማ የህዝብ መድኃኒት ቤት፤ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከ30ሺህ ለሚበልጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች አግልግሎት መስጠቱ የመድኃኒት ቤቱ ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ ተስፋነሽ ደስኖ ገልጸዋል። የመድኃኒት ቤቱ መቋቋም በመንግስት የጤና ተቋማት የማይገኙ መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ በቀላልና ተመጣጣኝ ዋጋ ገዝቶ መጠቀም እንዲችል ምቹ ሁኔታን የፈጠሩ መሆኑን ነው ስራ-አስኪያጇ የጠቆሙት። ወ/ሮ ተስፋነሽ…

Read More

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡ በዚህም መሠረት፦ 1ኛ.የ39ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔን መርምሮ አፅድቋል። 2ኛ.በመቀጠልም የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል።በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን 22 የግብርና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለመሰማራትከ 500 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ የቀረቡ ኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ…

Read More

ከቡና ወጪ ንግድ ከ2 ነጥብ 24 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት ውስጥ ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት ከ2 ነጥብ 24 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አለ። የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ሳህለማርያም ገ/መድህን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ ከ280 ሺህ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ ለመላክ ዕቅድ ተይዞ ነበር። በዚህም 409 ሺህ 605 ቶን ቡና በመላክ ከዕቅድ…

Read More

ባለፉት 11 ወራት ከ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ

መምሪያው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ደረጃ “ሐ” “ለ” እና “ሀ” ግብር ከፋዮች የግብር አሰባሰብ ንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፥ ዞኑ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ግብርን በተገቢው በመሰብሰብ የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ ነዉ ብለዋል። ለተግባራዊነቱም በዘርፉ የሚስተዋሉ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠርና…

Read More