ለሕብረተሰብ ጥቅም በሚሰሩ የልማት ስራዎች ሁሉም ትብብር ሊያደርግ ይገባል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። ለማህበረሰብ ጥቅም ከሚሰሩ ልማቶች በተጨማሪ የኢንቨስትመንት የልማት ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸው፤ እንደ ቴሌ ኮሙኒኬሽን፣ መብራት ኃይል፣ አየር መንገድ፣ የልማት ስራ በሚሰሩበት ወቅት 100 በመቶ ካሳ ይከፍላሉ ብለዋል። ነገር ግን ካሳ የሚጠየቅበት መንገድ ለምን ዓላማ? የሚለውን በደንብ ማለየት…
