“ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ናት፤ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን አንፈልግም” ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፤ ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ናት፤ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን እኛ አንፈልግም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ግን በጎረቤቶቿ መከበር አለበት ሲሉ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ እና የጎረቤቶቿ እሳቤ አንዳችን ለሌላችን በጣም አስፈላጊ መሆናችንን መገንዘብ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሰላም ካጣች ከተጎዳች…
