Trendings

Getenesh Gebeyehu

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሪዮ ዴጄኔሮ ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና በማንኛውም ሁኔታ የማይለያዩ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋሮች መሆናቸውን እንደተናገሩ ሺንዋ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኮሙኒኬሽን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በቱሪዝምና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባለብዙ ወገን ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዲያድግ ለማድረግ የሚያስችል…

Read More

የጽዱ ኢትዮጵያ፤ ጽዱ አካባቢ መርሃ-ግብር በቴፒ ከተማ ተደርጓል ።

በመርሃ ግብሩ የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች እና የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል። እንደ ሀገር ጽዱ ኢትዮጵያ ፣ጽዱ አካባቢ መረሃ ግብር ተቀርጾ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ሰነባብቷል ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም ይህ ኢኒሼቲቭ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እየተከናወነ ይገኛል። የዚሁ አካል የሆነው አካባቢን የማጽዳት ስራዎችን በማከናወን ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዞኑ ቴፒ ከተማ አስተዳደር ህብረት ቀበሌ የሚገኙ…

Read More

“ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለምአቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ የሰላም፣ የጸጥታ እና ዓለምአቀፍ አመራር መድረክ መክፈቻ ላይ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ስኬታማ ትብብርን ለማስቻል አፀፋዊ መተማመንን የሚያሳድጉ ዓለምአቀፍ ተቋማት የመኖርን አጣዳፊነት አንስተዋል። ዓለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት ይረዳ ዘንድ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅራቸው ምሉዕነት ባለው መልክ የሚሻሻልበትን ሁኔታም…

Read More

በክልሉ የዶሮ ርባታ ልማት እንዲስፋፋ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የሚዲያ ቡድን አባላት በዶሮ ልማት ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ወጣት ኑርሰላም ሀሰን እና ወጣት መሃመድ ካሳ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር በዶሮ ርባታ ስራ ከተደራጁ ማህበራት መካከል ናቸው። 3 ሆነው በመደራጀት ከጀመሩትን የአንድ ቀን ጫጩት ስራ ወደ እንቁላል ጣይ ዶሮ በመሸጋገር ውጤታማ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።…

Read More

ባለፉት ጊዜያት የተተከሉ ችግኞች የተሻለ የጽድቀት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አስታወቀ

በከተማ አስተዳደሩ የሚዲያ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ከመትከል ባሻገር የተተከሉትንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ሀገር አቀፍና ክልላዊ የሚዲያ ተቋማት በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል ። የሚዲያ አካላት በከተማ አስተዳደሩ ጋቡቃ መንደር በመገኘት ችግኝ የመትከልና በጽድቀት ላይ የሚገኙትን ምልከታ አድርገዋል። በምልከታው ወቅት ከ2014_2016 ዓ/ም ድረስ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው…

Read More

‎ኮሚሽኑ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ እውን እንዲሆን ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ

‎ ‎ኮሚሽኑ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ እውን እንዲሆን ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ ‎ ‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ 2017 ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና 2018 ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። ‎ ‎በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ…

Read More

የተጀመረው የሚዲያ የመስክ ምልከታ እውነታን ለህዝብ ገልጦ ለማሳየት ዕድል የሚሰጥ ነው ሲሉ የሚዲያ ባለሙያዎች ተናገሩ።

ባለሙያዎቹ ይህን ያሉት በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየለማ የሚገኘውን የበልግ እርሻ የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው። በክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባዘጋጀው የሚዲያ መስክ ምልከታ ሀገር አቀፍና የክልል ሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ። ከተሳተፉት ሚዲያዎች መካከል ጋዜጠኛ ቀደሰ ተክሌ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የመጡ ሲሆን እየተከናወነ ያለው የበልግ እርሻ አርሶአደሮችን ራሳቸውን ለመለወጥ የሚያደርጉትን ጥረት ይበልጥ አጉልቶ…

Read More

የሚዲያ ባለሙያዎች በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮው ባዘጋጀው የሚዲያ ቱር እየተሳተፉ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና አመራሮች በሚዛን አማን ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። በከተማው አማን ቀበሌ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ-ግብር ከሚዲያ ቱር ተሳታፊዎች በተጨማሪ መቀመጫቸውን ሚዛን ከተማ ያደረጉ ክልላዊና ሀገር-አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ባለሙያችና አጠቃላይ ሠራተኞች እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል። የከተማው ካንቲባ…

Read More

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ48ኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለሁለተኛው ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የእድገት ልማት ፖሊሲ ማስፈፀሚያ የሚውል 258,100,000 ኤስ.ዲ.አር እና ለፍጥነት መንገድ ልማት ድጋፍ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 27,300,000.00 ኤስ.ዲ.አር የፋይናንስ ድጋፍ እና የብድር ስምምነቶችን ለማጽደቅ በቀረቡ ሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ሁለቱም ብድሮች ከወለድ ነጻ፣ 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው ሆኖ የ6…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?

እንደምን ቆያችሁን ውድ አምባቢዎቻችን? ባለፉት ተከታታይ ወራት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ? በሚል አምዳችን  የስድስቱ የዞኖቻችንን ጠቀለል ያለ እይታ በወፍ በረር  ማስቃኘታችን ይታወቃል። ከእነዚህም ስለ ዳውሮ ዞን ባስቃኘናችሁ ክፍል በዳውሮ ዞን ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ተፈጥሮአዊና የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲሁም የዳውሮ ብሔረሰብ  ከሚታወቁባቸው ባህላዊ ዕሴቶች ዋና ዋናዎችን አቀርበን ነበር። ዛሬ ደግሞ ከነዚህ ባህላዊ …

Read More