በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ውጤታማ መሆናቸውን የታርጫ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ ።
በታርጫ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ያሉ የልማት ስራዎችን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ወጣቶቹ በተሰማሩባቸው የእንቁላል ጣይ ዶሮ በቀን ከ450 በላይ እንቁላል እያገኙ መሆናቸውን ለርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዷ በሆነችሁ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። የሌማት ትሩፋት አካል የሆነው የእንቁላል ጣይ…
