የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት እነማን ናቸው ?
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ የሚሳተፉበትን መድረክ ለማዘጋጀት እየተሰናዳ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኮሚሽኑም በሀገር አቀፍ እና በፌዴራል ደረጃ በምክክር ሂደቶች እንዲሳተፉ ከለያቸው ባለድርሻ አካላት አጀንዳ ለማሰባሰብ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቋል፡፡ በዚህ ሂደት ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ እና በፌዴራል ደረጃ ለሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ማህበራት፣ የፖለቲካ…
