የንጹህ መጠጥ ውሃ በማግኘት መደሰታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ የጌጫ ከተማና ጋቲባ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አግልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ያነጋገርናቸው የጌጫ ከተማና ጋቲባ ቀበሌ ነዋሪዎች በወረዳው የንጹህ መጠጥ ውሃ ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። በጌጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ የነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ጥያቄ ከመሆኑም በላይ ንጽህና ያልጠቀውን ውሃ ከተለያዩ ምንጮች በመጠቀማቸው ራሳቸውንና የቤተሰብ አባሎቻቸው በተለያዩ…
